የሻደይ በዓል የሰቆጣ አደባባዮችን አድምቋል።

0
37
ሰቆጣ: ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ አደባባዮች በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል።
“ዝክረ ሌተናል ጄኔራል ኃይሉ ከበደ” በሚል መሪ መልዕክት የሚከበረው የሻደይ በዓል በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በበዓሉም ከሁሉም የዋግ ኽምራ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የሻደይ ተጫዋቾች በልዩ የባሕል ጨዋታ በአልባሳቶቻቸው ደምቀው እያከበሩ ነው።
በበዓሉም የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ፣ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጌትነት እሸቱ እና ሌሎች መሪዎች የተገኙ ሲኾን የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎችም በዓሉን በባሕል አልባሳት ተውበው እያከበሩት ይገኛሉ። የሻደይ ባሕላዊ ጨዋታ ከነሐሴ 16/2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም ድረስ መከበሩን የሚቀጥል ይኾናል።
ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here