ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መናገሻዋ ከተማ ምንጊዜም ቢኾን ተናፋቂ እና ውብ ናት። ጎንደር ቱሪስት እና እንግዳ የማይለያት፤ በውስጧ አምቃ በያዘቻቸው የኪነ ሕንጻ ቅርሶች ምክንያትም ዓለም ሁሉ ሊያያት የሚጓጓላት መልከ ብዙ ናት። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ የሚከናወነው የቅርሶች እድሳት እና የኮሪደር ልማት የጎንደርን ያረጀ የመሰለ መልክ በመግለጥ እንደገና ሞሽሯል። ጎንደር በንጋት የምትፈካ፤ በምሽትም የምትደምቅ ውብ ከተማ ናት።
በአሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!