የጀማ ወንዝ ዳር የሎሚ ልማት

0
22
መስከረም 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
“አንሄድም ወይ ጀማ፣
ሎሚ ልናለማ” ተብሎ ተዘፍኖለታል። በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ ሞረትና ጅሩ ወራዳ በሎሚ ምርት የታወቁ ቆላማ አካባቢዎች ባለቤት ነው። በወረዳው በተለይም ጀማ ወንዝን ተከትሎ የተትረፈረፈ የሎሚ ምርት እንደሚገኝ የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ ይጠቁማል።
አካባቢው በአትክልትና ፍራፍሬ ብቻ ሳይኾን በሰብል ምርትም ከትርፍ አምራች አካባቢዎች አንዱ ነው። በእንስሳት ልማትም ቢኾን በተለይም የጅሩ ሰንጋ እንደሀገርም ታዋቂ እና ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው ነው።
ሞረት እና ጅሩ የውብ መልክዓ ምድር ባለቤትም በመኾኑ በቱሪዝም ጸጋው ተጠቃሽ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here