👉ከባሕር ዳር ከተማ ወረታ ባለው መንገድ ወረታ ሳይደርሱ ከዋናው መንገድ ወደ ቀኝ በመታጠፍ 19 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ የሚገኝ የተፈጥሮ ፍል ውኃ ነው።
👉ቀደም ብሎ በአካባቢው በስፋት የዋንዛ ዛፍ ስለነበር ዋንዛዬ የሚለውን ስያሜ አገኘ።
👉ፍል ውኃው እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ ሙቀት አለው።
👉ከመዝናኛ ማዕከልነት በላይ ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሕዝብ ሃይማኖት ሳይለይ የፈውስ አገልግሎት ይሰጣል።
👉 አምስት ገንዳዎች ያሉት ሲሆን የወንድ፣ የሴት እና የቤተሰብ ተብለው ተከፍለዋል።
👉በአራት ፈረቃ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ይሰጣል።
👉 በአካባቢው 357 ሔክታር አማካኝ ስፋት ያለው የተፈጥሮ ደን ይገኛል።
👉የግራር፣ ዋርካ፣ ባንባ፣ ዋንዛ የመሳሰሉ ሀገር በቀል እፅዋት በሚበዙበት ደን ውስጥ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ድኩላ፣ ሚዳቋ፣ ከርከሮ፣ ጥንቸል፣ ሰሳ የመሳሰሉ የዱር እንሰሳት እና የተለያዩ የአዕዋፍት ዝርያዎች ይገኙበታል።
👉በውስጡ ያለው እምቅ ተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ሲለማ ከባሕር ዳር እና ጎንደር ካለው አንጻራዊ ቀረቤታ ዋና የመዝናኛ ቱሪዝም ማዕከል በመሆን አሁን እያስተናገደ ካለው ከፍተኛ የሀገር ውስጥ እንግዳ በላይ የማስተናገድ አቅም ያለው ድንቅ መስኅብ ነው።