👉በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ከጣና ሐይቅ በስተደቡብ አቅጣጫ 167 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ካለችው ከግሺ ተራራ ስር ያለች የጠበል ምንጭ ናት
👉የአካባቢው ማኅበረሰብ ግሼ ዓባይ ምንጭ ብለው ይጠሯታል፡፡ ምንጯ ኩልል ያለ ውኃ የሚፈስባት እና ዙሪያዋ በቀርቀሃ ተክል የተከበበች ናት
👉የዓባይ መነሻ የሆነችው ምንጭ በአቅራቢዋ የቅዱስ ሚካኤል እና የዘርዓብሩክ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ
👉በሃይማኖታዊ ትውፊት የዓባይ መነሻ ከፍተኛ የፈውስ እና መንፈሳዊ ኃይልን ማጎናፀፍ የሚችል ጠበል እንደሆነ ይታመናል
👉ጥር 13 ታላቁ የግዮን በዓል በዓባይ መነሻ በሆነችው ሰከላ – ግሽ ዓባይ በድምቀት ይከበራል
👉ዓባይ የታላቅነት፣ የሥልጣኔ፣ የአንድነት እና የጽናት ምልክት ነው
ምንጭ፡- ቪዚት አማራ