ቦርከና የፍል ውኃ ኩሬ!

0
615

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጉዟችንን በአማራ ክልል ወደሚገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አድርገናል፡፡ አካባቢውን ቃኝተን ያለውን የቱሪስት ፀጋ ተመልክትን እናሳያችሁ ዘንድ ወደ ስፍራው አቅንተናል፡፡

ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ለቱሪስት መስህብ የሚኾኑ ሃብቶች ባለቤት ነው፡፡ አካባቢው ለዓይን የሚማርኩ እና አስደናቂ የተፈጥሮ ክስተቶችን በውስጡ አቅፎ የያዘ አካባቢ ነው፡፡በዛሬው ቅኝታችን የቦርከና የፍል ውኃ ኩሬን እንቃኛለን፡፡ የቦርከና ፍል ውኃ በደዋ ጨፋ ወረዳ በጀሮታ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ከከሚሴ ከተማ በስተደቡብ አቅጣጫ ነው የሚገኘው፡፡ አካባቢው ላይ ጠዋት ከተገኙ በጉም የተሸፈነ በመኾኑ ሰው ለመለየት እስኪያዳግት ድረስ የሚታይ ድንቅ የጉም ክስተትን ይመለከታሉ፡፡

ይህ የተፈጥሮ ጸጋ ፈጣሪ ያበጃጀው የሰው ልጅ ሊጠቀመምበት የሚገባው ድንቅ ሥፍራ ነው፡፡ ይህን አካባቢ በርካቶች ከመዝናናት ባለፈ በፍል ውኃው በመታጠብ ከሕመማቸው ለመፈወስ እንደሚጠቀሙበት በቀጣናው ጎራ ያለ ሰው መታዘብ ይችላል፡፡

ኩሬው እጅግ ማራኪ ለዓይን የሚስብ እና የሚማርክ ገጽታን የተላበሰ ስፍራ እንደኾነ የአካባቢው አስጎብኝ አቶ ታሪኩ አብደላ ይገልጻሉ፡፡ እንደ አስጎብኝው ገለጻ ቦርከና የፍል ውኃ ኩሬ ጥልቀቱ በግምት እስከ 2 ሜትር ይደርሳል ይላሉ፡፡

የፍል ውኃ ኩሬው አካባቢ አረንጓዴ እና ለዓይን የሚማርክ እንደኾነም ነው የሚናገሩት፡፡ ከቦታው የሚመነጨው ጭስ ጠዋት ጠዋት አካባቢውን በጉም እንደሚሸፍንም አስረድተዋል፡፡ ወደ አካባቢው ሰዎች በብዛት በመሄድ አካላዊ ተዝናኖት ያተርፋሉ፣ ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስም በፍል ውኃው እንደሚታጠቡ አስጎብኝው አብራርተዋል፡፡

በምሥጋናው ብርሃኔ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here