👉ከጎንደር ከተማ ማዕከል ሰሜን አቅጣጫ 9 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች
👉ከጎንደር ቀደምት መንደሮች መካከል አንዷ እንደነበረች ይታመናል
👉በተለምዶ የፈላሻ መንደር እየተባለች የምትጠራ የቀደምት ቤተ እስራኤላውያን መንደር ናት
👉ከጎንደር ደባርቅ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ የምትገኘው ወለቃ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገር ጎብኝዎች በምታቀርበው በዘመናዊ እና በባሕላዊ መንገድ የተሠሩ የሸክላ ምርት ውጤቶች በስፋት ትታወቃለች
ምንጭ:- ቪዚት አማራ መጽሐፍ