የእትጌ ምንትዋብ ቤተመንግሥት

0
484

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከጎንደር ከተማ ማዕከል በአማካኝ 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጉልህ ስማቸውን ጽፈው ካለፉ ሴቶች መካከል የእትጌ ምንትዋብ ቤተመንግሥት ይገኛል።

በደረሰበት ጉዳት ምክንያት የፈረሰው ቤተመንግሥት ከፋሲል ቤተመንግሥት በትይዩ ራቅ ብሎ ብቻውን የተሠራ ነው። የመኖሪያ ክፍሎች፣ የግብር አዳራሽ እና የንብ ቤትንም የያዘ ነው።

ቤተመንግሥቱ በድርቡሾች ጥቃት ጉዳት ደርሶበት እንደፈረሰ ይታመናል። ከቤተ መንግሥቱ ክፍሎች በተጨማሪ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ቅርሶች በቃጠሎ እና በዝርፊያም ጠፍተዋል።

የቤተመንግሥቱ ቅሪት አሁን ላይ ከእድሜ ጋር እየታገለ ይገኛል። አካባቢው ላይ ጎራ ላለ በቦታው ከሚገኘው ሙዚየም በርካታ ታሪካዊ ዕውቀትን ያገኛል።የቁስቋም ቤተ መንግሥት መሥራች እቴጌ ምንትዋብ የአጼ ባካፋ ባለቤት ሲኾኑ በዋናው የአጼ ፋሲል ግቢ ከባለቤታቸው እና ከልጃቸው አጼ ኢያሱ ሁለተኛ (ብርሃን ሰገድ) ጋር የኖሩባቸው ሁለት አብያተ
መንግሥታት እንዲሁም የሙያ ሥልጠና ሲሰጡበት የነበረው ቀጭን ፈታይ ግንብ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ድንቅ ምድር በተሰኘ ርዕሰ ካሳተመው መጽሐፍ የተወሰደ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here