አወይቱ ፍል ውኃ

0
197

👉ከአዲስ አበባ 260 ኪሎ ሜትር በአማራ ክልል ሰንበቴ ከተማ አራት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ እንፋሎት የሚተፋ ፍል ውኃ ነው
👉በሰንበቴ እና አጣዬ ወንዞች መካከል ይገኛል
👉ከፍል ውኃው የሚመነጨው የእንፋሎት ጭስ፣ የአካባቢው የመሬት አቀማመጥ እና የወንዞች ግንኙነት በአንድነት ለስፍራው ልዩ ውበት ሰጥተውታል
👉በተለይ ከድንጋይ ስር ከ9 በላይ ቦታዎች እየተነነ የሚወጣው እንፋሎት የቦታው ግርማ ሞገስ ነው
👉በሞቃታማው እንፋሎት ለመታጠንም ብዙዎች ወደ አወይቱ ይመጣሉ
👉የተፈጥሮ እንፋሎቱ አካላዊ መዝናናትን ይሰጣል
👉ብዙዎችም ከበሽታ እንደሚፈወሱበት ይናገራሉ
ምንጭ፡- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here