ዓለም ሳጋ ጥብቅ ደን

0
308

👉ደብረ ታቦር ከተማ ከመድረሳችን በፊት ከምናገኛቸው የተፈጥሮ ገጽታዎች መካከል አንዱና ቀዳሚው ነው።
👉ከባሕር ዳር መነሻውን ያደረገ ደብረ ታቦር ከተማ ከመድረሱ በፊት 12 ኪሎ ሜትር በፊት ደኑን ያገኙታል።
👉በፋርጣ እና በፎገራ ወረዳዎች መካከል ነው የሚገኘው።
👉ልምላሜ በማይለየው ደን ውስጥ የተለያዩ የእፅዋት እና የዱር እንሰሳት ዝርያዎች ይገኙበታል።
👉የደኑ ክልል ከሰኔ እስከ መስከረም ወር አጋማሽ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያገኛል።
👉የደን ክልል መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ኮረብታማ ሆኖ በየመካከሉ ሜዳማ ገጽታዎች ይስተዋሉበታል።
👉የደኑ ክልል ከመሬት ወለል በላይ ከሁለት ሺህ 180 እስከ ሁለት ሺህ 470 ሜትር ከፍታ ተለክቷል።
👉አማካይ የዝናብ መጠኑ አንድ ሺህ 300 ሚሊ ሜትር፣ አማካይ ሙቀቱም ከ15 እስከ 30 ዲግሪ ሴልሺየስ ነው።
👉በደኑ ክልል 124 የእጽዋት ዓይነቶች ይገኛሉ:: ከነዚህ ውስጥ 42 በመቶ የዛፍ፣ 29 በመቶ ቁጥቋጦ፣ 29 በመቶ ቅጠላ ቅጠሎች እንደሚገኙ ነው በአጥኚዎች የተለየው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here