የባቲ ገበያ

0
272

👉የባቲ ገበያ በባቲ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ከከተማዋ ጋር አብሮ የተመሰረተ ገበያ ነው
👉በሀገራችን ውስጥ ካሉት ረጅም ዕድሜ ካላቸው ታዋቂ የገበያ ቦታዎች አንዱ ነው
👉መጀመሪያ የገበያው ቦታ ወይራ ገንዳ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ የነበረ ሲሆን ለአመችነት ሲባል አሁን ወዳለበት አዲሱ ገበያ ዙሯል
👉ከብዙ አቅጣጫ የሚመጡ ሕዝቦች መገናኛ ነው፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የአርጎባ እና የትግራይ ብሔረሰቦች በአንድነት የሚገናኙበት እና ያላቸውን የሚገበያዩበት ቦታ ነው
👉ለገበያ የሚያመጡት ምርት፣ ባሕላዊ ቁሳቁሶች፣ አለባበስ እና አጋጌያጥ ለገበያው ልዩ ውበትን ይሰጣል
👉ይሄን የአገበያየት ባሕል ለመመልከትም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ገበያ የሚውልበትን ቀን ጠብቀው ባቲን ይጎበኛሉ
👉የባቲ ገበያ የሚውለው ሰኞ ቢሆንም ከዋዜማው እሑድ ጀምሮ እንግዶች ወደ ከተማዋ ይገባሉ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here