👉ከበግ ፀጉር የሚሠራ እና በካባ መሰል ቅርጽ ተዘጋጅቶ የሚለበስ ልብስ ነው።
👉በአብዛኛው የሚለበሰው በጣም ቀዝቃዛ እና ደጋማ በኾኑ አካባቢዎች ነው።
👉የእጅ ማስገቢያ እጅጌ እንዲሁም በቀኝ ትከሻ በኩል ወደ ላይ ቀጥ ብሎ የወጣ እና እንደጌጥ የሚያገለግል፤ የመሣሪያቸውን አፈሙዝ ደግፎ በመያዝ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
👉በተጨማሪ በርኖስ የሚለበሰው በሽምግልና ወቅት፣ ለጋብቻ ጥየቃ ጊዜ፣ በክብረ በዓላት ወቅት (ጥምቀት፣ ገና፣ ፋሲካ፣ በለቅሶ ወቅት፣ በተለይም ትልልቅ ሰዎች በሚያርፉበት ጊዜ) በአጠቃላይ በክብር ቦታዎች ላይ የክብር መገለጫ ኾኖ ይለበሳል።