የገታ አንበሳ ምሥል ድንጋይ

0
331

👉በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወረዳ ይገኛል።
👉ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ የአንበሳ ምሥል ነው።
👉የአንበሳው ምሥል በአየር ላይ የተንጠለጠለ ነው።
👉አብዛኛው የሰውነቱ ክፍል ግን ከዋናው አለት ጋር ተያይዟል።
👉ምሥሉ መቼ፣ በማን እና ለምን እንደተቀረፀ በውል የሚታወቅ ነገር የለም።
👉ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ለመሆኑ በምሥሉ ላይ የሚገኙ የተለያዩ መረጃዎች ይገልፃሉ።
👉በአንበሳው ምሥል ፊት ላይ የመስቀል ቅርጽ አለ።
👉ከጎኑ ደግሞ የሳባውያንን ፊደላት የሚመስሉ ቅርጾች ይገኛሉ።
👉አንበሳው ግንባር ላይ የሚገኘው የመስቀል ቅርጽ የአንበሳው ምሥል በክርስትና እምነት ተከታዮች የተሠራ ለመሆኑ ፍንጭ የሚሰጥ ነው።
👉የሳባ ፊደሎች ደግሞ የተሠራበት ዘመን ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ በገባበት ወቅት ሊሆን እንደሚችል ምስክር ናቸው የሚሉ አሉ።
👉መጠነኛ እንክብካቤ እና መጠለያ ተሠርቶለት አሁንም የሳባውያን ጽሑፍ እንደያዘ በቦታው ጎብኝዎችን ያስተናግዳል።
ምንጭ:-ቪዚት አማራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here