👉በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ፀጋዎች አንዱ ነው።
👉ደኑ ጎሽ ሜዳ፣ ወፍ ዋሻ እና ጓሳ በተባሉ የጉብኝት ሥፍራዎች የተከፋፈለ ነው።
👉በክረምት ወራት አዕዋፋት ስለሚበዙበት የወፎች መሸሸጊያ (ዋሻ) ተብሎ ይጠራል።
👉ጓሳ የሚገኘው በመሐል ሜዳ መዳረሻ ላይ ነው፡፡ ወርቃማው ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ እፅዋት እና ከአስራ አራት የማያንሱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ አዕዋፋት ያሉበት መኾኑ ቦታውን ልዩ ያደርገዋል።
👉በደብረሲና በኩል 7 ኪሎ ሜትር የክረምት ከበጋ ጥርጊያ መንገድ አለው።
👉ከ1929 እስከ 1932 ዓ.ም በጣሊያን የተሠሩት ሦስቱ የጣርማ በር ዋሻዎች የዚህ ደን አካል ናቸው፡፡ ከነዚህ ትልቁ 642 ሜትር ርዝማኔ አለው።
ምንጭ፡- የአማራ ክልል የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን