አምባ ፅጌ ገዳም – አስደናቂው የዋግ ኽምራ አምባ!

0
355

👉በኢትዮጵያ ከሚገኙ በጣም ጥቂት ማራኪ እና አስደናቂ አምባዎች ውስጥ አንዱ ነው።
👉በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ይገኛል።
👉በአካባቢው ብሎም በሀገሪቱ የሃይማኖት እና የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ የገዘፈ አበርክቶ የነበረው ታላቅ ስፍራ ነው።
👉የቦታው ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ቀጥ ብሎ የወጣ እና ማማው ላይ ደልዳላ ሜዳ በመሆኑ ለገዳማዊ አኗኗር ብሎም ለግዞት አምባነት የተመረጠ ስፍራ አድርጎታል።
👉አምባ ፅጌ የሚለውን ስያሜ የያዘው የማኅሌተ ፅጌ ደራሲ በሆኑት አባ ፅጌ ድንግል አማካኝነት እንደሆነ ይነገራል።
👉ከገናናው የዛግዌ ስርዎ መንግሥት መዳከም በኋላ በአባቶቻቸው አልጋ የቀደመውን ሰፊ የዋግ አካባቢ በራስ ገዝነት ሲያሥተዳድሩ የነበሩ ዋግሹሞች ለወኅኒነት እንደተጠቀሙት ታሪክ ያመለክታል።
👉በአምባው ላይ በርካታ ሃይማኖታዊ ቅርሶች አሉ።
👉አባ ጽጌ በዘመናቸው እንደተገለገሉበት የሚታመነው በዓይነቱ ለየት ያለ እና የግላቸው “በትረ መስቀል” አንዱ ነው።
👉የተለያዩ ጥንታዊነትን የተላበሱ መስቀሎች፣ የድንጋይ ላይ ስዕሎች፣ የተፈለፈሉ የውኃ ማቆሪያ ጉድጓዶች እና ሌሎችም በአምባው የሚገኙ ቅርሶች ናቸው።
ምንጭ: የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here