ያልተነገረለት የፌጎ ሐሪማ

0
258

👉በደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ በበቶ ወንዝ ዳርቻ ይገኛል።
👉በቆላማው አካባቢ ልምላሜን ተላብሶ የሚገኘው ፌጎ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) 35ኛ የልጅ ልጅ እንደኾኑ በሚነገርላቸው ሼህ አሕመድ አብደሏህ ከዛሬ 250 ዓመት በፊት እንደተመሰረተ ይነገራል።
👉መስጂዱ የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ሐረግ የኾኑት ታላቁ ሼህ አሕመድ አብደላህ መመስረቱ ጋር ተያይዞ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በልዩ ከበሬታ ይታያል።
👉ከእምነት ቦታነት በተጨማሪ የቁርኣን ትምህርት፣ ዚክርና መሰል ተግባራት ሲከናወኑበት ለረጅም ዓመታት ቆይቷል።
👉በዚህ ሐሪማ በየዓመቱ ግንቦት 18 እና 19 የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ ይከበራል።
የመረጃ ምንጭ ፦ ቪዚት አማራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here