በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የተያዘው የሎጎ ሐይቅ

0
276

ባሕር ዳር: ኅዳር 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ነው የሚገኘው – ሎጎ ሐይቅ።

ሎጎ ሐይቅ 23 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ስፋትና ከ70 እስከ 88 ሜትር የሚደርስ ጥልቀት አለው። በዞኑ ከሚገኙት አራት የተፈጥሮ ሐይቆች (አርዲቦ፣ ማይባርና ጎልቦ) በስፋቱና በጥልቀቱ ቀዳሚ ደረጃን ይይዛል።

ቀረሶ፣ አምባዛና ዱባ የተሰኙ ጣፋጭ የዓሳ ዝርያዎች በሐይቁ ይገኛሉ።

እጅግ ማራኪ የኾነ የውኃ ቀለም ያለው ሐይቅ ነው። የዓድዋ ጦርነት መነሻ የኾነው የውጫሌ ውል የተፈረመበት “ይስማ ንጉስ”፣ የመጀመሪያው የመውሊድ በዓል የተከበረበት “ጀማ ንጉሥ” መስጅድ፣ ግማደ መስቀሉ የሚገኝበት “ግሸን ደብረ ከርቤ”፣ ጥንታዊው ጫሊ መስጅድ፣ “አርዲቦ” ሐይቅን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ባሕላዊና ታሪካዊ የቱሪዝም ሐብቶችም በሐይቁ ቅርብ ርቀት ይገኛሉ።

ሎጎ ሐይቅ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ (ዶ.ር) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት ውስጥ ተካትቶ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገለት እንደሚገኝ ከደቡብ ወሎ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here