አንኮበር

0
279

አንኮበር
ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትካለለው አንኮበር የተመሰረተችው በ1733 ዓ.ም ነው፡፡ መሥራቿ የሸዋው ነጋሲ መርሐ ፅድቅ ደጅ አዝማች አምሃ ኢየሱስ (1733-1767 ዓ.ም) ናቸው። ከደብረብርሃን ከተማ ምስራቃዊ አቅጣጫ 42 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

አንኮበር የሰለሞን ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት የድንኳን ከተማ ነበረች። ዋና ከተማነቷ ወደ እንጦጦ እስከዞረበት እና ኋላም አዲስ አበባ እስከተቆረቆረችበት ድረስ አንኮበር ለስድስት የሸዋ ነገሥታት በማዕከልነት አገልግላለች።

በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተሾሙት ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ (1806-1840 ዓ.ም) ደብረብርሃን የተቀመጡት በጣም ለአጭር ጊዜ ሲሆን ዋነኛ መሠረታቸው ያደረጓትም አንኮበርን ነበር። በመልካም ዘመኗ አንኮበር የበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የውጭ ሃገር ጎብኝዎች እና ደጅ ጠኚዎች መናኸሪያ፤ የሃገሪቱ የወህኒ ቤት እና የመንግሥት ሥርዓት መማሪያ ትምህርት ቤቶች የነበሩባት፤ አብያተክርስቲያናት እና የመንግሥት ህንፃዎች አምረው እና ደምቀው የሚታዩባት ከተማም ነበረች።

የንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ወራሽ ንጉሥ ሐይለመለኮት ዘውድ በጫኑበት ዘመን አንኮበር በአፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት ተወረረች። አፄ ቴዎድሮስም በቦታው ድንኳን ጥለውም ቀናትን አሳለፉ።

በ1870ዎቹ ከምኒልክ መመለስ በኋላ እንደገና ተቋቁማ የጥንት ማዕረጓ ተመለሰ። በሶስት ከፍተኛ አምባዎች ላይ ተመስርቶ ሞቅ ደመቅ ብሎ የነበረው የመንግሥት ማዕከል ወደ እንጦጦ በመዛወሩ ምክንያት አንኮበር እየቀዘቀዘች የነበረ ቢሆንም አሁን ደግሞ ሞቅ ደመቅ ማለቷን ቀጥላለች።

ምንጭ፦ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች መጽሄት

(ታምራት ሲሳይ)
በኲር ታኀሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here