ቲፋሻ ፏፏቴ!

0
262

ባሕር ዳር: ሐምሌ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቲፋሻ ፏፏቴ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ የሚገኝ እጅግ ውብ እና ማራኪ የቱሪስት መዳረሻ ነው፡፡ ፏፏቴው ከወረዳው ዋና ከተማ ማክሰኞ ገበያ በሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሥፋራ እንደኾነ ከወረዳው ባሕል ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በጠገዴ ወረዳ ማክሰኞ ገበያ ባሕል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዘርፌ አበበ እንደነገሩን አካባቢው እስካሁን በሌሎች ታውቆ የቱሪስት መዳረሻ መኾን አልቻለም። ነገር ግን የአካባቢው ማኅበረሰብ የሚዝናናበት ድንቅ ሥፍራ እንደኾነ ነው ያብራሩት፡፡
ኀላፊዋ አካባቢውን በማልማት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ መሠራት እንዳለበት ገልጸዋል። ይህን ሥፍራ ለማልማት ጥረቶች መቀጠላቸውን አስረድተዋል፡፡

2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ የሚምዘገዘገው ቲፋሻ ፏፏቴን ማልማት በቱሪስት ልማቱ ዘርፍ አካባቢውንም ኾነ አማራ ክልልን ተጠቃሚ እንደሚያደርገው ነው የገለጹት፡፡ ይህን የቱሪስት መዳረሻ ለማልማት በመንግሥት በኩል ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ በአካባቢው የቱሪስት ማረፊያ ሎጅ እና መሰል መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ባለሃብቱ እንዲሳተፍም ኀላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አካባቢው እንዳይለማ ባለፉት ጊዜያት ተጽዕኖ ሲደረግበት ስለመቆየቱ የሚናገሩት ወይዘሮ ዘርፌ አካባቢው ነጻነቱን ካወጀ ማግስት በኅብረተሰቡ ተሳትፎ አካባቢውን ለማልማት ጥረት እየተደረገ መኾኑን አብራርተዋል፡፡ አካባቢው ላይ ያሉ ጸጋዎች እንዳይታወቁ የቀድሞው ሥርዓት መረጃዎችን የማጥፋት እና የማውደም ሥራን በስፋት ሠርቶ ቢሄድም ከአካባቢው እድሜ ባለጸጎች መረጃዎችን እየጠየቁ ለማደራጀት እየተሞከረ ስለመኾኑ ነው የገለጹት፡፡

በቅርብ ጊዜም አካባቢው ላይ የተደራጀ መረጃ እንዲኖር እየተደረገ ነው ብለዋል። ቅድሚያ መልማት ለሚገባቸው የቱሪስት መዳረሻዎች ቅድሚያ በመስጠት እና በማልማት ለተጠቃሚው ክፍት ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ ነው የነገሩን፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here