ወረኢሉ

0
284

👉በደቡብ ወሎ አሥተዳደር ዞን ከደሴ ከተማ 91 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ናት
👉ቀደም ባለው ጊዜ የብዙ ነገሥታት መናገሻ እና የቤተ አማራ ማዕከል ነበረች
👉ከ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በፊትም አካባቢው ዋስል ከተማዋ ደግሞ ምድረ ሀጓ ተብለው ይጠሩ ነበር
👉በታሪክ የወረኢሉ ስም ጎልቶ የሚነሳው ዳግማዊ ምኒልክ ለዓድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ ባሳዋጁበት ጊዜ “ዘመቻዬ በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ” በማለት ሠራዊታቸውን በአንድ ማዕከል እንዲሰባሰብ የመረጧት ቦታ በመኾኗ ነው
👉በዘመኑ በብዙ ሺህ ለሚቆጠረው ሠራዊት ቀላል የጦር መሣሪያዎችን በመሥራት እና ለዘመቻ የሚኾን ስንቅ በማዘጋጀት በዓድዋ ለተመዘገበው ድል ግንባር ቀደም አስተዋጽኦ አበርክታለች

ምንጭ፡- የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here