👉በታላቁ የጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ከዓባይ ወንዝ መውጫ ላይ የተመሰረተች ናት
👉የባሕር ዳር ስያሜ እና አመሰራረት ከጣና ሐይቅ ጋር የተሳሰረ ነው
👉የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋና ከተማ ናት
👉ከአፈ-ታሪክ በተጨማሪ በጽሑፍ የተረጋገጠና ብዙዎች የሚስማሙበት የባሕር ዳር ታሪክ የሚጀምረው በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው
👉በአነስተኛ ጎጆ ቤቶች እና በውስን ሰዎች ምስረታዋን አድርጋ ቀስ በቀስ እያደገች የመጣችው ባሕር ዳር ወደ ምልዑ ከተማነት ለማደግ ረጅም ዓመታትን ወስዶባታል
👉ከተማዋ በሁለተኛው የጣሊያን ወረራ (1928-1935 ዓ.ም) ብልጭ ብሎ ከነጻነት በኋላ በነበሩት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጠለው ወርቃማ የእድገትና ውበት ዘመን የከተማነት ቅርጽ እንድትይዝ፣ የተለያዩ ተቋማትና ፋብሪካዎች እንዲገነቡባት በማድረግ መሰረቷን አጽንቷል
👉ዓይን በሚያጠግብ ውበቷ፣ በዓባይና ጣና ባለቤትነቷ፣ በቀደምት ቅርሶቿ በአያሌዎች ተመራጭ ከተማ እንድትኾን አድርጓታል
👉ከአዲስ አበባ በሞጣ መስመር 485 ኪሎ ሜትር፣ ከአዲስ አበባ በደብረ ማርቆስ 563 ኪሎ ሜትር፣ ከደሴ 462 ኪሎ ሜትር ከላሊበላ 312 ኪሎ ሜትር፣ ከጎንደር 174 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች
👉ሰፋፊ ባለዘንባባ ጎዳናዎቿ ለእንግዶችና ለኗሪዎች ነጻነትና ምቾት የሚለግሱ ናቸው
ምንጭ፡- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ