በአንድነት ፓርክ ውስጥ የሚገኘውን የአማራ እልፍኝ በአዲስ ለመሥራት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ።

0
193

ባሕር ዳር: መሥከረም 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአንድነት ፓርክ ውስጥ የተገነባው የአማራ እልፍኝ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ወደከተማዋ ሲገቡ በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈጥሯዊ፣ ባሕላዊ እና ታሪካዊ የመስህብ ሃብቶችን ለማሳየት ይረዳል። ሃብቶችን በምስልና በቅርጻ ቅርጽ በማሳዬትና ገለጻ በማድረግ ቱሪስቶች ወደ አማራ ክልል መጥተው እንዲጎበኙ ታሳቢ ያደረገም ነው።

እልፍኙ ከአሁን በፊትም አገልግሎት እየሰጠ የቆየ ሲሆን የበለጠ ክልሉን ሊገልጽ የሚችል እልፍኝ በአዲስ መሥራትና ገላጭ የሆኑ የቱሪስት መስህቦችን በተገቢው መልኩ ማሳየት ተገቢ ነው። የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው ይህን ሥራ ለመሥራት የቢሮው አመራሮች እና የሥራ ክፍል ኀላፊዎች በቦታው በመገኘት በቀጣይ ሥራው ሲከናወን ምን ጉዳዮችን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ምክክር ተደርጓል። የባለሙያዎች ቡድንም በቦታው በመገኘት ዲዛይን እንዲሠራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here