ጎባጢት ድልድይ

0
169

👉በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከእንፍራዝ ከተማ በቅርብ ርቀት ይገኛል
👉ከ457 ዓመታት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል
👉ያለምንም ብረት ከኖራ ብቻ የተሠራ ነው
👉በአጼ ሰርፀ ድንግል ዘመን በ1560ዎቹ ነው የተገነባው
👉በእንፍራንዝ ከተማ እና በታሪካዊው የጉዛራ ቤተ መንግሥት መካከል የጋርኖ ወንዝ ላይ የሚገኝ ነው
👉ርዝመቱ 12 ሜትር፣ ቁመቱ 9 ሜትር፣ ስፋቱ ደግሞ 4 ሜትር እንዲሁም ውፍረቱ 1 ሜትር ነው
👉ጉዛራ ቤተመንግሥት እና እንፍራዝ ከተማም በቅርብ ርቀት ማዶ ለማዶ የሚገኙ ሲኾን፤ በተለይም በክረምት ወቅት ወንዙን መሻገር የማይቻል ነበር
👉የአጼ ሰርፀ ድንግል ባለቤት እቴጌ ስነወርቅ ማርያም ከጉዛራ ወደ እንፍራዝ ልደታ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይቸገሩ ስለነበር ያን ታሳቢ ተደርጎ እንደተሠራ ይነገራል
ምንጭ፡- ቪዚት አማራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here