ወላዲት ዓባይ ሰከላ!

0
358

የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ መነሻ ናት። ሰከላ የወለደችው ዓባይ ወንዝ በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰከላ ወረዳ ከግሽ ተራራ ስር በምንጭነት ፈልቆ ነው ሀገራትን እያረሰረሰ ጉዞውን የሚቀጥለው። ዓባይ በገባር ወንዞች እየፈረጠመ ጣና ሐይቅን ከፍሎ ያልፋል። ኢትዮጵያን እንደ መቀነት እየዞረ ጉዞውን ወደ ሜድትራንያን ባሕር ያደርጋል፡፡

ከተራራው ሥር የሚፈልቀው ምንጭ ፈዋሽ እንደኾነ የሚታመነው የአቡነ ዘርዓብሩክ ፀበል በመሆኑ ለበርካታ የእምነት ተጓዥ ጎብኝዎች መናኸሪያ ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡

ዘወትር ወር በገባ በ13ኛው ቀን የአቡነ ዘርአብሩክ ክብረ በዓል ነው። በየዓመቱ ጥር 13 ደግሞ ዓመታዊ የንግሥ በዓሉ በመኾኑ ወላዲተ ዓባይ ሰከላ ከፍተኛ የቱሪስት ቁጥር ታስተናግዳለች፡፡ Visit Amhara የመረጃ ምንጫችን ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here