በጃዊ ወረዳ የሚገኘውን የባኩሳ ብሔራዊ ፓርክን ይጎብኙ፦
የባኩሳ ብሔራዊ ፓርክ፦
👉በክልሉ ምክር ቤት ሰኔ 1 ቀን 2004 ዓ.ም በደንብ ቁጥር 96/2004 ዓ.ም በዝክረ-ሕግ ጋዜጣ ታትሞ ብሔራዊ ፓርክ ሆኖ ጸድቋል
👉51 ሺህ 796 ሄክታር ስፋት አለው
👉80 በመቶ በላይ በተፈጥሯዊ ደን የተሸፈነ ነው
በውስጡ የያዛቸው
👉ከ28 በላይ ታላላቅ አጥቢ የዱር እንስሳት
ከ31 በላይ አዕዋፋት
👉ከ63 በላይ ዛፍና ቁጥቋጦዎች እና በርካታ የሳር ዝርያዎች
👉የተለያዩ የእባብ፣ ዘንዶ፣ አዞና የመሳሰሉ ተሳቢዎች ይኖሩበታል
👉ከእፅዋት ዝርያዎች መካከል ሽመል፣ ጥቁር እንጨት፣ የቆላ ዋንዛ፣ ኮመር፣ የእጣን ዛፍ፣ ዶቅማ፣ ላሎዋርካ እና ሾላ ይገኙበታል
👉 ከእንሰሳትና አዕዋፍት ዝርያዎች መካከል አንበሳ፣ ተኩላና ብርቅዬ የሆነችው ሶረኔ ቆቅ የፓርኩ ልዩ መገለጫዎች ናቸው
ምንጭ: የአማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ