ባሕል እና ወግን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ኪነ-ጥበብ ሚናው ከፋተኛ ነው።

0
127

ደባርቅ: ታኅሣሥ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ስድሥተኛው የባሕል እና ኪነ-ጥበብ ዓውደ ርዕይ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ነው። አውደ ርዕዩ የባሕል ትስስርን እና ትውውቅን ከመፍጠር አኳያ ጉልህ ሚና እንዳለው ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።

ኪነ-ጥበብ የማኅበረሰብን ወግ እና ባሕል ከማስተዋወቅ አንጻር የማይተካ ሚና እንዳለውም ተገልጿል። የሰሜን ጎንደር ዞን ተወካይ አሥተዳዳሪ አደራጀው ባዘዘው ባሕል እና ወግን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ እና ማኅበራዊ እሴቶችን ለማጎልበት ኪነ-ጥበብ ሚናው ከፋተኛ ነው ብለዋል።

የባሕል እና ኪነ-ጥበብ ዓውደ ርዕይ ተተኪ ከያኒያንን ለማፍራት እና ለማበረታታት ቁልፍ መንገድ ነው ያሉት ደግሞ የሰሜን ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ አስራት ክብረት ናቸው።

በዓውደ ርዕዩ ለመሳተፍ ከተለያየ አካባቢዎች የመጡ የባሕል ቡድን አባላት፣ እርስ በርስ ለመተዋወቅ እና ልምድ ለመቅሰም እንዳገዛቸው ገልጸዋል።

በዓውደ ርዕዩ ላይ ከዞኑ ወረዳዎች የተወጣጡ የባሕል ቡድኖች እና ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here