ባሕር ዳር: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደጋዋ ንግሥት እንጅባራ ከተማ በጥር ከሚደምቁት የአማራ ክልል ከተሞች አንዷ ናት።
85ኛው አንጋፋው የአገው የፈረሰኞች በዓል እየደረሰ ነው። ፈረሶቻቸውን እንደሰው ልጅ በማዘዝ ተመልካችን “አጀብ” የሚያሰኙ ፈረሰኞች ጥር 23 በእንጅባራ ይከትማሉ። በዚህ ቀን የሚቀር ፈረስ እና ፈረሰኛ የለም።
ዓመታዊ በዓሉ በተለየ ድምቀት ይከበራል። በበዓሉ ላይ ተገኝቶ መታደም ልዩ ሀሴትን ይሰጣል። አሚኮ ዲጅታል ሚዲያ ሁነቶችን በሙሉ በሁሉም የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ለተከታዮቹ ያደርሳል። ቤተሰብ እየኾኑ ይጠብቁን።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!