የአማራ ክልል በድምቀታቸው፣ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳቸው እንዲሁም ጎብኝዎችን በመሳብ አቅማቸው የተለዩ ድንቅ ክብረ በዓላት መገኛ ነው።
የታኀሣሥ መጨረሻ ቀናት እና የጥር ወር ደግሞ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ድንቅ ክብረ በዓላት የሚከበሩበት ወቅት ነው። ዘንድሮም እነዚህን ክብረ በዓት በድምቀት ለማክበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነው።
እርስዎ በየትኛው ክብረ በዓል ለመታደም አስበዋል?
1 – ታኅሣሥ 26-30 የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከአስዳማሚው የቤዛ ኩሉ ሥነ-ሥርዓት ጋር – በላሊበላ
2 – ጥር 6 የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የልደት በዓል – በጎንደር
3 – ጥር 10 የከተራ በዓል – በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በምንጃር ሸንኮራ፣ በባሕር ዳር እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች
4 – ጥር 11 የጥምቀት በዓል – በጎንደር፣ በላሊበላ፣ በምንጃር ሸንኮራ፣ በባሕር ዳር እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች
5 – ጥር 12 የዘገሊላ በዓል – በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች
6 – ጥር 13 የግዮን በዓል – በሰከላ ወረዳ – ግሽ ዓባይ
7- ጥር 14-15 ጥርን በባሕር ዳር – በባሕር ዳር
8 – ጥር 18 የሰባር ጊዮርጊስ የንግሥ በዓል – በባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች
9 – ጥር 21 የአስተርዮ ማርያም በዓል – በግሸን፣ በመርጡለ ማርያም፣ በደረስጌ እና በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች
10 – ጥር 23 የ84ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ክብረ በዓል – በእንጅባራ
11 – ጥር 25 የመርቆርዮስ በዓል – በደብረ ታቦርና በእስቴ መካነ ኢየሱስ ይከበራሉ። እርሰዎም የክበረ በዓላቱ ተሳታፊ ይሁኑ! መረጃው የቪሲት አማራ ነው
ፎቶ– ከአሚኮ አርካይቭ