2011 ምሬት አሜታዳ ጄሜራማ ቴግባርሾ ቱስቱኽ አምሉ አሻሪው ሜርሃ ግብር ዴኑሳ እሳንቶ ዴሜክጝዴስ ጃላ እምፕልታቕ ይኮኖሚስ ቴኬምስታንታ ዝኩኽ ታምብ ኬፍንኹ አኽⶓ ጉዋንጉዊ ወረዳዉ አሬሳቻንትካ ዲብሱና::
አማኻሪ ክልልታኪላ 2018 ምሬት አሜቱ አምሉ አሻሪውሳ ሜርሃ ግብሮ ጄሜርፅጙ ቴርት “ቴስፌ ቴኬልንስ” ናው ቹዋ እንፅኼንትስ አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂ ጉዋንጉዊ ወረዳ ትሩብርሃን ኬቤሊዳ ኬፍቴንካ እንፅኺኩ አላፍካስታ አሬሳቻንትካ አግስቱኑዳ ካስጛ::
ቤዴራስኩ አሜትካዳ ይቶፒያው ዴኑ ሜቴን 40 ታፋ ሊኽዴስ ይቪቺ እሺኹ አኽⶓ ግብርኒው ሚኒስቴርዴስ አግፅንኹ ንቫር ቶኬሜ:: እንጚኪላ ፍትሬቱሳ አብቶ ሊሚፃውላስስታ ብቴ አንኬባኬባማ እሜውላ ይጉጙ ምክንያታስ ዴኑ ሽፋን ሹኻ ታፋ ሊኽሾ ዜሬቕ ናማ ሲጊፃው አችዳ ታምባሼ::
እንጚኪላ ምግቡ ዋስትኒው ችግርሾ ሚፃሺኹ አኽጝ ታክስስቴ:: እሳ ችግሮ ኽይጝስ ይቶፒያዳ 2011 ምሬት አሜታዳ ጄሜራማ አሜት ቺፋ ቢሊዮንስ ቼፍስታንኩ ችግኝካ ቴኬልስትካማጊ አሬሳቻንትካውስታ አጌራው ይኮኖሚ ኪሴ ሜዜጌብፅጝስ ካላው አችሾ እንዝጜ ፄዋማጊ አግስቴ::
አምሉ ልማቱ ሜርሃ ግብርስ ቴኬምስታንትካ አኽጝስ ይስካማ እንፃኽስቴካማጊ አግስታንኩ አሬሳቻንትካዴስ ትሩ ብርሃን ኬቤሊው ዝኩዋንቲ አቶ አብታሙ አጋሉ እምፕልያኽ:: ፌዩንኩ አሜትካዳ ክሴሎ ኬሴልፅጝስስታ ዴንስ ያኻውሳ ችግኞ ቴኬልጝዴስ ድምክና አቮካዶ ቴኬልካ:: ይኮኖሚውሳ ትክሞኪላ አግፄካ:: ዲከረንስ ችግኞ ቴኬልካማ ኽብፂውሳ አሉምቶ ዙርፅጝስ ሴብሉሳ ምርቶኪላ ኬሽጝፅካማጊ አኽⶓ ድኹዌካ::
2018 ምርቱ ዝቤንዳ እምፕል ኩፅ አኹኪ ውጋቢ ብቲዳ ምስሊስ ቴኬልጝስ ሜጋቢት አርፊዴስ ጄሜርካማ ፍሮ ግሽጝስስታ ኮንፖስቶ ብቲዳ ቤቴንጝስ ቴርታኒስ እጂⶓ አቶ አብታሙ ዲብስካ:: ውማይቴንካው ውማዩ ድጋፍኪላ ክርፂ አኽⶓ ጉሽካ::
ዳጉፄ ዜሬካማጊ አሜት ቺፋ እሌቱ ኬሌብስ ያኻውሳ ይቪቼ አግፃሺንኩ ያኹኒውላ ዊዳፊ ትክምስስታ አብቱ ልግስኒስ ጉሽፃ ያኼ ንካማ አምኑኑሳ አቮካዶ ቴኬልካማ ኬሻንቴ ምርቶ አግፅጝስ ቴግባርሾ ቱዌካ::
ዊዛሩ አሰረሳች እርትባንኪላ ሲዚ ኩፃ ብቲዳ ቴኬልጝዴስ ቤዴራ ቴክልስ ያኻውሳ ብቴ ሜጋቢት አርፊዴስ ጄሜርካማ ቴርስጝስ እሊኩ አሬሳቻንትካሊ ምስሊስ ቴኬልካ:: ቤዴራ አሬሴካማ እሌትስ ያኻውሳ ምርቶ አግፃሺንኩ ያኹኒውላ አግፃኑ ምርት ኩፅኒ ልቓ አኽጝስ ድኽትዴስ ፊጝስ ቼጌርስታሺንኩ አኽⶓ ቶኬምካ::
ዊዛሩ አስረሳች ኑኑውስታጊ ናካዳ ጛዋ ውልጅኒ ቻኒትጛማጊ ያኹኒው ካላኑ አክምስጊ ቴኬሉኑሳ አቮካዶ አንኬባኬብካማ አግፃኑ ምርትዴስ ኪሴ ሜዜጌብፅጝስ አኬድⶓ ዙሜካ:: አቮካዶ ቴኬላማ ቴኬምስትኹ ዴስ እንዴስ ቤዴራ እሺያስኩ ያኹኒውላ ውማይቴኑ ክንቲስ ኩፅኒ ካንቴ ኪስካማ እንፅኼ ጄሜርⶓ ቶኬምካ::
ጉዋንጉዊ ወረዳ ትሩ ብርሃን ኬቤሊው ግብርኒ ፅፌት ጝናሱ አላፊ ሰዋገኝ የኔጌት ጛሾስ ሴብሎ ሊሚፅጝስ ቼጌርፃው፣ አሉምት ቺንችጙስትኹስታ ኩሪስ ሺሽርስታውሳ ብቴ ጎሌልካማ ዴንስስታ ምግብስ ያኻንኩ ችግኙ ፌልካዋ ቴኬልጝስ አሬሳቻንትካዋ ውማዩሳ ክንቴ አግፃንታ ፄውስቱኽ እንፅኺስ አምሉ አሻሪው ቴግባር ይስጛማ ሲፍⶓ ጉሽካ::
2018 ምርቱ ዝቤንስኪላ ኬቤሊታ ሊኽ ሄክታር ብቲዳ አቮካዱሳ ፌሎ ምስሊስ ቴኬልጝስ እክድ እምሰታማ እምፕል ጌርክስ 54 ሄክታር ብቲዳ ቴኬልስትⶓ አቕፄካ::
አቶ ሰዋገኝ ኑኑዉስታጊ ቴኬልስትኹ አቮካዱ ፌላኻዳ ጉባሬ፣ ሚትሚታዋ፣ ስንዳዮ፣ ጅንጅብሌስታ ኮረሪማዋ ሊሚፃንታ አሬሳቻንትካስ ክንቴ እይካማጊ አኽⶓ ጌሌፅካ:: እንዳ አሜትዳኪላ 20 ኩንታል ጉባሪው ዜሩ ፌል ቴርትⶓ ጉሽካ:: አምሉ አሻሪው ልማት ኬቤሊታ ክርፂ አችዳ አግስታው አኽጝስ አሬሳቻንትካው ኩርፄንትኪላ ጋሺስታው አኽⶓ ቶኬምካ::
ጉዋንጉዊ ወረዳ ግብርኒ ፅፌት ጝናሱ አላፊ አቶ አበባው አምሳል ጛሾስ 2018/2019 ምርቱ ዝቤንዳ ዴንስ፣ ትክልቲስ፣ ኩፓኩፒስስታ ክምካው ሜኑሳ ያኻውሳ ችግኙሳ ፌሎስታ ቴኬልጝስ ያኻውሳ ብቴ ቴርስጙ እንፅኺ ቤዴራማ አኮሜችስቱስ እጂኹ አኽⶓ ጉሽካ::
ቡኑ፣ አቫካዱ፣ ሙዙ፣ ማንጉውሳስታ ሜኑስ ያኻውሳ ዴኑ ችግኙሳ ፌሎ ቴርሴካማጊ ቴኬልስታው ዙራሙሪሾ እንዜጝትጝፄካማጊ አግስታንኩ አኽⶓ ጉሹንኩ አቶ አበባው 1 ሻይ 100ዴስ ጃላ ሄክታር ብቲዳ ቴኬልጝስ እክድ እምስታማ ቴግባርሾ ቱስትⶓ አቕፄካ::
104 ሄክታር ብቲዳ ዴሜካ ምስሊስ አኹኪ ክላስተርስ ሊሚፅጝስ እንፃኽስስታማጊያኽ ንካ:: 270ሻይዴስ ጃላ ቡኑ ፌል ቴኬልስታው ዙራሙሪሾ እንዜጝትጛማጊ አኽⶓ ጌሌፅካ::
አቶ አበባው እይኑ ጊሊፂዳ ወረዳታ እንዴስ ቤዳራ አቫካዶ ምስሊስ አኹኪ ክላስተርስ ሊሚፅጙ ዴስ እላቲው እሺኹ አኽጝዴስ ፌይኹስ ቴጋናኻዳ ሹኻስታ ሴዛ ዜራሺንኩ አሬሳቻንትካውሳ ካንቴ ኪስጝስ ታሪክስ አቫላምቲ ያኹኽ 54 ሄክታር ብቲዳ እምፕል ጌርክስ ምስሊስ አቮካዶ ቴኬልጝስ ካሊስትⶓ አቕፄካ::
አምሉ አሻሪው ልማትስ እዝብ ካንትፅኹ ኩርፄንትስ ምስጋኔ ዲግሱንኩ አቶ አበባው እሳ ዜጌቤ ቴርስንኹሳ ወክቶ ኺስታ 650 ሄክታር ብቲዴስ ጃላ ወረዳታ ችግኝ ቴኬልስትⶓ ቶኬምካ:: ፍንሾስኪላ ይስጝፃማ ቴግባር ስፍፅጝስ እክዶ ሳኪትጝፃማ እምፕልታቑሳ ይኮኖሜ ሌጌፅጝስ እንፃኽስስታው አኽⶓ አቕፄካ::
አዊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂ ግብርኒ ሜምሪዉ አላፋ ዊዛሩ ቤዛዊት ጌታሁን ጌሌፁኑዉስታጊ ብሄረሰቡ ቺፅጝፂታጊ 110 ሚሊዮን ያኻውሳ ችግኞ ቴኬልጝስ ቤዴራ ቴርት አሌድስታማ ቴግባርሾ ቱስታ::
ዊዛሩ ቤዛዊት ኑኑዉስታጊ ዴንስስታ ምግብስ ያኼካማ ይኮኖሚውሳ ኪሴ ሜዜጌብፃንኩ ችግኙ አይኔትካ ቴርቴካማ ቴግባሮ ይስጝፅጝስ እንፅኺሾ ቱስትⶓ ቼሜትጝፄካ:: ብሄረሰቡ ቺፅጝፂው ኽብፂው አይኔትሊስታ አይር እግልታሊ አስሜምጛውስታ ፄዴክጙ ሜቴን ኬፍቲኒ ያኹኽ ችግኝ ቴኬልስታማጊ አኽⶓ እርዳትፅካ::2 ትኩሚ 7 ሚሊዮን ያኻው ቡኑስታ ኩፓኩፒው ፌል ቴርታማ ቴኬልስታማጊ አኽⶓ ቶኬምካ::
ንግስቴ ተስፋ


