ቺዛጙ ተረው ፃግብጂቱ ዊርየው አቚዙ አልስን

‎ወይ ኽምረ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰኒዙ ዊር የው አቑዝመ ችጝሽተትነይድ ቃልሽታንድ 52 ላይስ የጝ። ብሄረ እቅ ጭሰጭሰንዙ አቑዝቊ ችብረጥድ ቺተቺተቊ ፍጥርቊዝመ እጅር ሰራሸተ ችግሰጥዝ ፊትንሸጛጙ አቕሽም እኔንት ችበችብርጝ ዲቈነውዝ እቀ ኽቭርድ ዊርየው አቚዙ አሩሸተ ጻቨናንስ ሰራሽተው ሰቭድ አትር ቃጽልኩ።

‎‎ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰን አቒል ችጝሸቊ ላጝጠ ወረጥዝመ ሊጘ ኻትመ ጭሰጭሰንጢስ ድሃነ ወረደ ጻግቭጂ ወረደስመ ዝቛለ ወረደ ቀሰው ፋጽምጽመ ጽየቊ ወረደጥ አቐነውድ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰንዙ አቑዝመ ኢነርጂ ቃወነድ 2017 ዓ.ሰ ኻለይዙ ፋጽምጽመድ ጊምግመው ኮሪዝ አርቒስኩ።

‎‎ይንም ንጭቱ ጽፈሽዝ ቺተቺተቊ ወረድጢል ጽበው አቑዙ ትንዝሽትን ችጝሰድ እክሰናስ ሰራሽታጙ ችጝሸው ሰቭድ አንቭቭስነ ቀኑን።

‎‎ምጝግስትስመ ቀሰው ጻቨቊ ድርጅተንዝ ጋቭ ሰራሽተቊ አቑዝቁ ችብረንጥድ ሰራሽ እቀኽቭሪዝ ዊርየው አቑዙ አልስን ጻቨነውድ ትኽኑ አቐው እቀ ኽቭር ፋጥረነዊስ ጋብ ችጘርድ አውግረው የጝ።

‎‎ቃውሰዝ ዊግስነቊ አት ምስጋናው አዳነ ዝቛለ ወረደ 01 ቀቨሊዙ ጽበተ አጛንድ ጛይም “አቑ እጝቅ ሩሄ ጽየው ገቨይዝቅ ተሚሰተ አቐነዊዝ ድኽዝመ ጻጀ ጉሬ ቲዛው እርወ እንቅዝቅ ተሚሰተ አቐው አርወ ጽየው የጝ የነውዝ ጝታ ጅውነይዝጘ ጽበው አቑዙ ትንዝሽትንድ ጋልጽጛንድም” አቚዝ አርወ ችጝንቅ የነው ምነነ ቀቨው እቀ ኽቭር ዊኑ ንጭቱ ሊጘ ምት ጂመይዝ አቑዙ አርወ ችጘነው ጡውሸኩ ይሽት ዚምናንዝ ዊነው ይነ ዋቕረድ እክሰ ችጝንኩኑን “የነውዝ እን ሊጘ እርፍ አቒዝ ትራንስፎርመር ቃጥልሹዝ አውግረው ችግሰይል ሊቨነውዝ ፍልፍልዙ አቑ ዝይጛጙ ኮሌራ ይሽተው ጽውዘዝ አጋልሽተነው ቸልጘጘን ዊግትጝኩጙ።

‎‎አቑዙ አርወድ አርቐቅ የነዊስ ጐው ሚስማርዝ ጣዘነውዝመ ቺተቺተው ገቨ ጻቨነውዝ ጨቅጛጙ ችጝሸቊ አካለንድ አርወድ ልብሰነውዝመ ኻየነውዝ ነን ጽበው አቕንቲዝ አቑ እንቅ ጅወንጢል ችጝጠ ማጥን በንትድ ፈራቓጙ ተርኩ ይጝኩጙ።

‎‎አት ደረጀ ይልማ ወይኽምረ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰን ድሃነ ወረደ 022 ጭላ ቀበሊዙ ጽበተ አጛንድ ጛይም ጝታ ቀበሌይዝጘ 2016/ 17 ጫረዙ ኮሪዝ ዊነው ስወይዝ ምላሠን ዝቨድ ኻዴነውዝ ኩረዝመ ላጥ ችግሰንጥዝ ምላሠን ፍጥሩ ኻደገዝ ቈይሽጛጙ አቐጘ ጋልጸነውዝ ቺተቺተቊ ከቨጥ ድርጅታንዝመ ምጝግስትጅቅ አቐነውዝም ቲክንክነ ጻቨነውዝ እቀ ኽቭርድ ትኽነድ ኻይሽትጠጘ ቸለው አቕንትድ ሰራሽታጙ አቐጘ ዋርዝጘኩ “ምጝግስት ሰራሸቊ አቑዝቊ ችብረንጥድ እቀ ኽቭርድ ይው የጝ የው አምነነውዝ ጨቅሽጛንድም ወረደይዝ በውዝ ሪፖርት ጻቨነውዝ ሰራሽትጥጘ የጝ ጻቭሽታጙ ጽበውድ ሙየ ጒይጥድም አጝሽ ሳልጥጝ ተረነውዝ ጨቅሸው ገቨድ ጻግነነውዝ ሰራሽጛጙ የጝ”

‎‎አቑዝቊ ችብረንጥድ ፍጥሩ ኻደገዝም አነ እጅር ኹር ፋጥረው ችግሰዝ ምላሠን ኮር ጨቨቅ ጨቅሽጛጙ ችጝሽጘኩ።ችግሰድ አክሰናንስም ሙየ ጒጥ ጋብዝ  ቀሰው ጐነጐን ጽበነውድ የጝ አትደረጀ ዊግትጘዉድ።

‎‎ ላየ ዊግስነይ ዊዝር በለጡ ደሴ ጻግቭጂ ወረደ ጻተ ኻትመዙ ጽበተ ዊግትጛንትጘም አቑ እጀው አቐነዊዝ ዊርቨዙ አቑድ  ዝይጛንድ ቺተቺተው አቑ እኹረጥ ጽውዘንጥዝ አጋልሽትጛጙ  አቑ ተምዝንዝ ዊርቨ ፊርጛንድም አቕሽ ጝታ ጊዝድ በክናጙ ዊነጘ ጉየነውዝ ነን ጽበው አቕንቲዝ አቓንድ ይጘኩ”አቑ ይና መድራቒል ችጝናንስቅ ይናት ሸጘ አቕን ኩኑን። እጉርትጘም ዊርቨዙ አቑ ዝያይንም ጽውዘድም አቕሽ ድዝኩ”እጉር ዊንጘው ገጠሪስ ፍጝ ኻትመይል ጥውጘውድ ቺዝየው ገቨ ተምዝንመ ሊግዝትዝ አቓንስቅ ጝታጝን ድውስጘው አቑ ተምዘቊ አቐነዊዝ ቅልጥፈዝ አቚድ ችጛንስም ዋቕርጘኩ፡፡

“ሰራሽተቊ አቑዝቊ ችብረንጥድ አውስም አቒጝቀስ ይናግስ አቐነውድ ልብትን እጅር ጨቃየጘድ ፍጥሩ ኻደገዝም ቈይሻይጘጘድ እቀኽቭርድ ጥወጥውሽትን ሰራሽናጙ የጝ። ያን ይቕመ ትጘን አቑ ይጝኒል ድውሰነውዝ ዝይንዙ ዊር የው አቑ አሩሸነዊስ ከስጘ ይ እንግርነይል አትክልተን ቲክል ዝይሰነው በናንስቅ ድውጥጘ ማጥን ዋቕራጙ የጝ” የነውዝ አቑዝቊ ችብርጥድ ጨቀው አውማው አካልድቅ ጡውሸውዝ ሽሹዳጙ እዳቐቊ ሰባንድም ሰራሽትጥጘ ጡውሸኩ ይጛንድም ዊዝር በለጡ ዊግትጝኩጙ።

‎‎ጻግብጂ ወረደ አቑዝመ ኢነርጂ ጽ/ጝን ዲቈተ አት ሞገስ ክብረት ዊርየው ዝይንዙ አቑ የነት አዊንም ዳቐዳቕኒስ ናጸ አቐው እንሰስዝመ እቅ ዝይጘውድ ቺተው አቑ የነት የጝ። እቅ ጻጘው ዊርቨይስ ቐዳቐነዊስ ቺዝ የው ባምቦዝመ ጝዊርተድ ኻይሽተው እንሰሲዝመ እቂዝ ጝታለ ቺዝን ሰራሸነውዝ አሩሽጥጘ ጻቨነው ቸልሻንድ የጝ።

‎‎ዊርየው አቑዝየነው ቸልሸውድ ይጘትግረ” ወረደድ ጣይትንዝ ንቕጸቊ አቑዝቊ ችብረንጥድ ፋይርጝ ዊንጛንስቅ ብሄረ እቅ ጭሰጭሰኒጅቅ ዊግሸነውዝ ጽንኸ ጻቭሽት  ሰቪዝጐ ጥውጝ ዞኒስ ይውሽትጘው 32 ባምቦን ጻግነናንስ አቓንድ ይን ግነ 55 ባምቦን ጻግነነው ቸልንኩኑን። አይጥ አቑዝቊ ችብረጥ 4 አጥጘ ሰራሽን ኩኑን”ይጛንድ ዊግትጝኩጙ።

‎‎እኔንት ጻቨነውዝ ወረደይል ጽበው አቑዙ ችጝትነይድ 42.7ላይል ችጝሽተጘድ ሚዝረድ ቓሊሰኩ። ብሄረ እቅ ጭሰጭሰኒዙ አቑዝመ ኢነርጂ ዲቈተ አት አብርሃም አሰፋ ጝታ ጋቢዝ በጀትዙ አምረይዝ 629 አቑዝቁ ችብረጥ ቀለውዝ ማኽለኘዝመ አውግረው ጻግንን ጻቨነውዝ ዊርየው አቑዙ ችጝትነይድ ዊነው40 ላይስ 55 ላይዝጐ ንየስ የነው ቸልሽትኩ።

‎‎እን የንትም ጻቨናንስ ምጝግስትዝመ ምጝግስትቊ አየቊ ድርጅተኒዙ ከቨድ አውግረው ዊነነውድ የጝ ጋልጽጘውድ ” አቑዝቊ ችብረንጥድ ጨቅሽጛጙ አምረ ጨቨቅ ጻግነነውዝ ላየ አይር በጀት ዋቕረቊ አቒጝቀት ዚልቅትነይ ጻየቊ አጥጘ ማጥን ሰራሸነው በንዘኩ ምጝግስትተስ ኻይሽተውድ ሰራሸነው ጭቚ አይጝቀስ ሰራሸተቊድ ኻይሽትጛንስ ልብትን ፋጥረነው ጡውሸኩ። እቀኽቭርድም ጝትኽነድ ሊሚስጠ ማጥን አቑዝቁ ችብረንጥድ ጡውሸውዝ ሰራሸነው ጡውሸኩ ይጝኩጙ”

‎አቑ አውማው አው ሩሄ ጽየው ገቨይዝቅ በንዘው አቐውዜ እጅር ኹርዙ ትኽነድ ኻይሽትጠ ቸለውድም ጝዊርተድ ኻይሽተው አቑ አሩሸነው ጥውሻንድ የጝ።

‎‎ ጥቅለ ኻግሪዝጘድ20/30 % እቀ ኽቭር ዊርየው አቑ አሩሽጠጘ ኻለይ ጻቭሽት ሰራሽታጙ አቐውዜ ቺተቺተቊ አቑዝቊ ችብረንጥድ ጥውሸውዝ ኻየነው ዳቐቊድ ቈሽ ዋቕረነው ሳልጥነው እቀ ኽቭርዙ ጋልጽሽተነ አቓንስቅ ወይቱ ጅውነይል ጽበቊ አቑዝቊ ችብረንጥድ ኻየነው እንቅ እቀ ኽቭሪስ ኻይሽተው ቲግቭር አጠ ጡውሸኩ።ይና እጻ ጻቭናጙ ሲነቭሽኑን።

አመልማል ተድላ

ታኽሳስ 15/2018

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna