ዜገን ፃቭጘው ትኽነ ኻይን ምርምረዙ ደግምግመድ ቓልሽታንድ ኻግሪዝጘድ፣ እድሚዝጘድ፣ ትኽነዙ አቕንቲዝጘድ ቺተቺተቁ ጛይ።
አቕሽም አልም አቅቨ ተግዝ ገሪየኑ ኽክምነዙ ምርምረዝ ጅሉዘ ፃረቊዙ እግዝግዘይዝ 2025 ዓ.ስ ፃቭሽተው ፅንኸድ ደቡብ ኮሪየቱ ኽዝቨን ግሪየኑ ኽክምነዙ ምርመረ ፃቨነውዙ ጝተ ዲዝገትድ አጉረው አቓንድ ፊንላንድ፣ ስዊድንስመ ኔዘርላንድትል ፅበቁ ዜገንዙ እግዘድ ሳስየው የጝ።
ኢትዮጵየም ፃረቊዙ እግዝግዘይዝ 2022 ዓ.ስ ደቡብ ጎንደርትል ፃቭሽተው ላው ፅንኸ ሚሪየዊዝጘ 40.2% አቐቁ ዜገን ገሪየኑ ትኽነዙ ምርመረ ፃቭጝኩⶔ።
ይና ኻግሪዝጘም አቑ ወይቱ ጅውነይዝጘ ቓልናንድ ኽክምነ ፊርጝ ትኽነዙ አቕንትድ ደድሰነውዙ ዲዝጝትድ ሳስየው የጝ።
እኒዙ ኽየው ምላሰንድም ችብረንጥዙ ችጝሽተትነይዙ እጅጝትዝመ እቀኽቭሪዙ አቅምዙ ችግሰድ የጝ።
ዜገን ትኽነዙ አግልግለዝ ፊስጘው አጉረተ ፈንዝ ምላሰን አጉረው ድኽትዝጎ ሊቨነዊስ ከስጘ ቓደነው ቸለው ፅውዘዴት ኪፍለነው ጊንዝቭ በነውዝ ንቕፀቁድ ጝተ ሩሔድ ብነጘኩ።
እንዝ ምላሰንም እቀኽቭሪል ፅበው ጛስ ጛይቱ ከቨከቭሽትንዙ ባኽልድ አትርዘነውዝ እክሱ፣ ዊርተዝመ ዚልቀትነይ ፃየው እጝቅጥቅ አቅቨው ትኽነ ቓዝንዙ አግልግለ ዜገንዝ ችጝሽተተ ፃቨነው ላው ኻግርሸንቱ ፖሊሲ አቕኲ።
ኢትዮጵየቱ ፌደራል ዲሞክራሲው ሪፐብሊክ ኽገ ምንግሥት አንቀጽ 55 እጥን-አንቀጽ (6) ሲሪየ እቀገረደ ትኽነ ቓዝንዙ ቕየ ፍ ፃድቅኲ።
ሰሃለ ሰየምት ወረደ መሸኻ ትኽነ ጣቭየ ኽክምነዙ አግልግለ አሩሸተ ዊዝር የሻለም ደርሶስመ አት ገብርወ ካሳየ እቀኽቭርድ ፊስጛጙ ዊንጘው ተሚትየቁ ኢኮኖሚዝመ ገረዱ ፈንጢስ ትኽነ ቓዝንዙ ስረትድ እዳዘነው ቸለጘ ዊግትጝኩⶔ።
አት ገብርወ ካሳየ እቀገረደ ትኽነ ቓዝንዙ አቫል አጘት አኰ እምት እጊስጛጙ አቐነውድ ጉይጝ ጝዝ በውግ ኽክምነዝ ፊስጘው ፈንድ አጉረው ዊነጘድ ጋልፅጝኩⶔ።
“ይና ጝነቁድ ፅዊትጝ ኽክምነ ፊስናንድ ፊስናጙ ዊነው ፈንድ አጉረው የጝ ዊነውድ። አቅም በነውዝ ፅዊትን ኽክምነዝጎ ፊራይነውድ የጝ ንቕፃጙ ዊነውድ። ትኽነ ቓዝንዙ አቫልነይዝ ግረ ግነ ኪፍልነው ዊቱ ፈንዝ ጥውሸው ኽክምነድ ችጝናጙ የጝ “ይጘኲ።
እቀገረደ ትኽነ ቓዝንዙ አቫል አጘት ሻቘ እምት ፃየቁድ ዊዝር የሻለም ደርሶ ጝታ ጋብዝ ቀለው ጊንዝቭዝ ኽክምነድ ቸጘነው ቸለነዊስ ከስጘ “ይ ጝነቁድ ፅዊትጘንድ ቃዝየውዝ ኽክምነ ፊሰነውዙ ዲዝጝትድም ዲዝጝጨ ፃቭኩ” ይጝኩⶔ።
ውርም እኰ እቀገረደ ትኽነ ቓዝን አቫልነይድ እጝቅትነይዙ ትኽነድ ኻየናንስ አጉረው አርወ ፃየው አቐነውድ ልብትጛጙ አቐነውድ ጋልፅጝሽም ትኽነዙ ችብረንጢል እትለቁ አግልግለዙ ቢተንጥድ እኪትጛንስም ዋቕረ ጉየነውድ በርየቁም።
ትኽነ ቓዝንዙ ካርድድ ፃይጘት እግርገ ኽክምነ ጣቭየይዝጎ፣ ሆስፒታሊዝጎ ኽክምነዙ አግልግለ ችጘናንስ ፊርጘው ኰሪዝ ጝተ ፅውዘይዙ አይንቲዝጘ ጥላ እቻይሽተቅ የነውዙ ቢተ ፅበነውድ አርቒስጝኩⶔ።
ኽዝቭድ ቢዘይል ፍ ጝሉ ፋርማሲየንዝመ ችብረንጢል ጥላድ ጅቨነውዝ ጥውሽትየው ፈንዝ አጋልሽትጛጙ አቓንስቅ ሚሪሸው አካልድ ችግሰድ እክሰነው ጥውሸው አቐነውድ ዋቕርጝኩⶔ።
ሰሃለ ሰየምት ወረደ ትኽነ ጽ/ጝንዙ ደርግቭሸተ ዲቈተ አት መንግስቱ መኳንንት ወረደይዙ እቀ ኽቭርድ ትኽነ ቓዝን አግልግለዙ አርወድ ውርቑጠ አቐነውድ ልብት ጝትኽነድ ኻይጠ ቸልሰው አርቕት ፋጥርንዙ ሰቭ ሰራሽተነዊዝ አጉረው ፈንጥ ተርጘጘድ ዊግትጝኩⶔ።
ነንቱ ሰቲዝም ጝቕም ኽዝቭድ ትኽነ ቓዝንዙ አግልግለድ ተምዝ ችብረይዝጎ ተራጙ ፅበው አቕንት ፋጥርሸነውድ ሚሪጝኩⶔ።
እን በጀት አምረይዝ ኪፍለጥ እቀኽቭርድ አጉረተ፣ ማኽልኘዝመ ሳስየው የነውዝ ሻቘ ተግዝ ኪፍለነውዝ እቀኽቭሪዙ አቅሚዝጘድ ኪፍልሰናንስ ኻሊሽት ሰራሽታጙ አቐነውድ አርቒስጝኩⶔ።
2017 ዓ.ስ ወረደይዝጘ 6 ሽኽዝ 619 እቀኽቭሪዙ ክፍለኒስ 7.5 ሚሊየን ቁርሽ አኽቨነውዝ እቀገረደ አቅቨ ትኽነ ቓዝንዙ አርውሸጥ ፃቨነው ቸልሸነውድ ሚሪሽኲ።
እን አምረይዝ ቈሽ 7 ሽኽዝ 8 ላዝ 38 እቀኽቭሪዙ ክፍለን ፃጀጒይጥ 3 ሽኽ፣ ማኽልኘ ተጊል ችጝሸቁድ 2 ሽኽ፣ ሳስ የው ተግል ፅበቁድ ቈሽ 1 ሽኽዝ 500 ቁርሽ ኪፍልሰናንስ ኻሊሽኲ።
አቅም እጀቁ እቅድ ቺዘነውዝም ናፀ ኽክምነዙ አግልግለ ችጝጥጘ ማጥን ሰራሽታጙ አቐነውድ ደርግቭሸተ ዲቈተድ አርቒስጝኩⶔ።
ኽዝቭድ ፍቃድኘ አቕ ኪፍለው ጊንዝቭዝ ቈሽ ጥውሸው ኽክምነዙ አግልግለ ችጝጠ ማጥን ክልልዝመ ኻግር አቅቨ ትኽነዙ ችብረንጢጅቅ ቲስመምን ፊስጘጘድ ጋልፅጝኩⶔ።
“እጝቅ ይና ዞኒዙ ችብረንጥጅቅ እንዝጘም አዲስ አበባትል ችጝሸቁ ቺተቺተቁ ኽዝቭዙ ፋርማሲየን፣ አይደር፣ ፈለገ ህይወት፣ ጎንደርት ተከቁ አጉረቁ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታለንጅቅ ቲስመምን ፊሰነውዝ እቀኽቭርድ አግልግለ ችጝጠ ፃቭናጙ የጝ” ይጝኩⶔ።
ወረደ ተግዝም ኮሚኒቲ ፋርማሲ ብዘነውዝ እቀኽቭርድ ትኽነ ቓዝንዝ ጝ ጅውነይል አቕ ጥውሸው ኽክምነዙ አግልግለ ችጝጠጘ ፃቨናንስ ወረደይዙ ጭሰጭሰን ምኽር ጝኒጅቅ ማኽርጛጙ አቐነውድ አት መንግስቱ አርቒስጝኩⶔ።
አውማው እጅርድቅ ትኽነ ባንድ ጭቑ አየውም ኽክምነዙ ችብረንጢዝጎ ፊረነው ጥውሸውድ። ጝትኽነድ አርቐናንስ ገሪየኑ ኽክምነዙ ምርመረ ፃቨነውዝ ቲክንክነ ፃቨነው ጥውሸኲ።
ኽክምነዝ ፈው ፈንድ ገውተነውዝ ጝንል አቕን ፅውዘዝ ናን ይወነው እን ዚምንዙ ኹሪስ ኻይሽታውም።
አቓንስቅም አውማው እቀኽቭሪዙ ክፍልድቅ እቀገረደ ትኽነ ቓዝንዙ አቫልነይዝ ኪፍልሸው ፈንድ ኰሪዝ ኪፍለነውዝ ጝመትም አቑ ጝነቁድ አውማው ፅውዘይስ ማኽተነው ጥውሸኲ።
ሳምራዊት ግርማይ
ታኽሰስ 30/2018




