ምነነ ቀቭየቊ ውሸቭል !

‎ጅርቊ ፍርዘነው  ኻግር ተግዝ ቲኩርት ይውሽታጙ ተረውዝመ ቀሰው ሊግዝት ነሰናንስ አርወው አቐጘ ቺተቺተቊ እግረ ጋጸንድ ልብስጘኩ።

‎‎ ላው ጅርቊ ፍርዝጠ ኻሊየው እጅር ቲክነቊ ገበንድ አርቕጠ ኻይሽተኩ፤ቃውሰይዝ ጅርቊ ፍርዘናንስ ውርቑጠ በነኩን?ውርቑጠስ አብዘኩ? የውድ አርቐነው ጥውሸኩ። ጝዝለም ጅርቊ ፍርዝንዙ መለንድ ልብትን ሰቪዝጐ ጥወነው ተሚሰኩ።

‎‎እን አቒስም ጅርቊዙ አይንተንድ የነትም ቕሉን ማለጥድ፣ ስየዝ አቐቊድ እኒዝጘም ቕሉንዝመ ስየይዝ አቐቑድ አርቐነው ላው ጅርወ ፍርዘተይስ ልብትን ኻይሽተኩ።

‎‎ አቓንስቅም ጅርቁዙ ዚረንድ ቺዘነው ዊስነተ ቲግቭር የጝ የነት የጝ። ተክዘዝ ጻረቊ ጅርቊ አልምቱ ኻግረኒል ቕሉነ ማለነውዝጐቱ ቀሰቊ ጛይ ይሽተኩ።ቃዚጝ ሊግዘቊዝመ ደየቊ ጅርቊም ጽብጘጘ ዲዝጝትዝመ አንቭቨነውዝ ልብተነው ቀሰው የጝ።

‎‎ስየዝም ቕሉነዝም አቐቊ ጅርቊ ላው አምረ አቒዝ 240 ቕሉን አጢስ ማለነው ቸለቊጛይ ይሽታንድ እን ኮሪዝም ግልወ ጅርወ 3.4  ኪሎ ግራም አቓንድ እውነሸን ቈሽ 2 ነቁጠ 95 ኪሎ ግራም ችጘው ስየዝ ዲነነው ቸለቊ አጛንስቅ ተሚተቊ ጻቨኩ።

‎‎ይንም  ንጭቱ ጽፈሽዝ አምደወርቅ ኻትመል ጅርቊ ፍርዝን ሰቪል ውላቕጝ ፈንቊ አቐነው ቸለቊ ውሸቭሊዙ ሚኩርሽንድ አንቭቭስነ ቀኑን!

‎‎ጅርቊ ፍርዝንዙ ቲግቭርንድ ጅርቊዙ ሸድ ተሰነዊስ ኪርመኩ።ኹረዝመ ቀሰው ብጣ ማርጸነው ላየ ሰቭ አቓንድ ጨጭን ፍልፍልዘነ ዚምኑ ማሽንም ላው ዊስነተ ገቨ የጝ።

‎”እያሡ ስመ  ያሬድ ላው ግሬዙ ጨጭን ሊጊሰነ” የው ገረደድ፣ 2011 ዓ.ስዝ አኰ ውሸብል ተገተግሽትጝ ጅልውልወተ እድወዝ ችጝሸው 1ሚሊዮን ቁርሽዝ ኪርምጘው ሰቭ የጝ።

‎‎ኰሪዝ ላው ግሬዙ ጨጭንድ ሊጊሰነውዙ ሰቭል ውላቐቁ   ውሸብልድም ህውሓትቱ ጣይትንዝመ ቺተቺተቁ ምላሰንጥዝ ኪሰረል ችጝጝ ዊንⶔ። በውግቱ አብቁተ ነንቱ ጸደይ ባንክቲስ እድወ ፊሰነውዝ ሰቭ ኪርመቊ አቓንድ ጅርቊዙ ፍርዝን ወየድ ኪብረውዝመ ጻየ ጻይሽተቊ ፈንጢ ጅቅ 1 ሚሊየን ጊንዝቭ ፊስጝኩጙ።

‎‎ እን ጊንዝቭድ እድወዝ ተረው ዊናንስቅ ኮሪዝ ፊስጘው ፈንድ ንቕጸውዝ ጽበጘ አቕ ሰቭድሞ ሩድየውም ዊኑ። ኮሪዝ ጅቭሽተቊ ቕሉንድ ፊልፍልሽጝ ጥውሸው ጨጭንዙ ጊቭርት ችጘናንስ ቸልሽየውም ።

‎‎ገረደይዙ አቫለኒስ ላውድ ገረደይዙ ፃፈተ ውሸብለ ሀይማኖት ሙሉ “ኰሪዝ ቕሉን አልሰተዙ እጅጝትዝ ማሽንድ ሰቭ ችብሰነዊዝመ ህውሓትቱ ጣይትኒዝ ኪስርን ዊንሽም፣ እግርገ ዊቱ ጊንዝቭዝ ምነነ ቀቪጝቀት ሰቭድ ቃፅለነውዝ ይነ ቢንድ ዊስን ቺዝየው ፅብን ፅብናጙ የጝ” ያንድ ዋርዝኲ።

‎‎ላው ሚሊዮን እድወዙ ቢንድ ዊሰነውዝመ ጝተ ጝንድ ቃወነዊስ ከስጘ እን አምረይዝ ፍርዝጘቁ ሻቘ ሽኽ ጨጭኒስ 1 ሚሊዮንዝ ንየ ቁርሽ ተነነው ቸልጘጘድ ዊግትኩ። እኔን ቈሽ አቭርድንዝ ሰቭተነውዝመ አምርቱ ምነነድ ቀቪጝቀት ሰራሽጘው ሰቪዝ ተረው ፈን አቐነውድ የጝ ጋልፀውድ።

‎‎ላየ ጅርቁ ፍርዝንዝ ተገተግሽተቁ አቫለኒስ ውሸብለ እለኒ ሙሉ ሰቭ ኪርምሻንድ ዲዝጝሽጥዊል አሽ ግርቭዝመ ጊንዝቭዙ ኪሰረም ዊንጠ ቸለው አቐነውድ ጋልጽርኩች።

‎‎”ሰቪል ፅበው እጅር ላው ግሬ ብሽ ላው ግሬ ችጘነውድ እዳቓውም፣ አትርን ሰራሽናንስቅም ቺዝየው ጊንዝቭ ተነነው ቸልንኩኑን” የች።

‎‎ጅርወ ሊጊሰነውዙ ሰቭድ አቑ ዚሰነው፣ ዀሰነው፣ ዊርሸነውዝመ ጝተ ትኽነድ ኻየነዊስ ኪርም ጥውሸው ቲክንክነ በነው የጝ፤ በውግ ኪሰረ ዊንሽም አቫለንድ ሲለቲጝቀት ሰራሽጘው ሰቪዝ  ቢንድ ኪፍልጝ ነን ቺዝየው ፅብኒል ችጝሽጘውድ ሚንውትዝመ አትርጝ ሰቭትጘው ሰቭዝ አቐነውድ የጝ።

‎‎ሰቭትረው ሰቪዝም እቀጘዝ እምጥጝረይ አረጘድ ጉይር ተረዊዝ ጅርቁዝ አቐው ኹረዙ ማሽንድ ጅቨነውዝ ፈራዝጝ ሰራሸቁ አቐነውድ ውሸቭለ ኢሌኒ ጉይርኩች።

‎‎”እያሱስመ ያሬድ ላው ግሬዙ ጨጭን ሊጊሰነ ገረደ” ነንቱ ሰቲዝ 5 ሽኽዝ 500 ጨጭን ሊጊሰነዊል ችጝሸው አቓንድ ምጝግስትቊ አየቁ ድርጅተኒጅቅ አርየዙ እፅቁፅቈ ፋጥረነውዝ ተረው ሊጘ እርፍዝ 700 ሽኽ አልተው ትርፍ ችጘናንስ ሰራሽጛጙ ችጝሽጘኩ።

‎‎ሰራሸው እጅር ምነነ ቀቭጠ ጥውሻውም ኪሰረዝ ኪርምጘው ሰቭድ ነን ላጥ ውሸብሊዝም ሰቭዙ አገነ ፋጥርጛጙ ችጝሽጘኩ።

‎‎ድሃነ ወረደ እንሰስ ፃጀ እፍርት ጽ/ጝንዙ ጓነ ቃወተ አት ካሳ ታረቀ ጝተ ጋብዝ ውሸብልድ ሰቭዙ ቀንት ፃየቁ አቐነውድ ሚሪጝ፣ አኰ አቫለንዝ ኪርምሸው ገረደድ ነን 22 ግልቁ 29 እቁን ጥቅለዝ 51 ውሸብልዝ እን ዚርፍዝ ሰቭዙ አገነ ፋጥርሸነውድ ጋልፅጝኩⶔ።

‎‎2011 ዓ.ስ ወረደይዝጘ ጅርቁ ፍርዝንዝ ሻቖ ገረደ ተገተግሽት ዊንሽም ፃውተዝመ ቺተቺተቁ ምላሰንጥዝ ኪስረነዊዝ ምላሰን ሊጘ ገረደንድ ፋይርጝ ዊንጘጘ ሚሪጝ ነን “እያሱስመ ያሬድ ላው ግሬዙ ጨጭን ፍርዝን ገረደዙ አቫለን ጝተ አትርኒዝ ንቕፀቁ ውሸብል ሰቭዝጎ ዋጥርዘነው ቸልሸነውድም ጋልፅጝኩⶔ።

‎‎ገረደድ እንዝ ንየ ፈኑ ፃቨናንስ አርሽነይ ጽ/ጝንድ ትኽነዙ ሙየ ጉይጢጅቅ አቭርደነውዝ ጥውሸው ሙየዙ ከቨ ፃቭሽታጙ አቐነውድ ጉይጝ አልምቱ ባንኪስ ሊጘ ሚሊዮን ከቨ ፃቨነውዝ 51 ውሸብልድ ላብጠ ተገተግሽትጝ ሰቭትጝጥጘድ ፃቭጘጘድ ጉይጝኩጙ።

‎‎ገረደይዙ ሽጙድም “ፃጀ ላብጠዝ ጅርወ ፍርዝን፣ ቕሉንዙ ጊቭርትዝመ አሪሽን አቭርድንዙ ገረደ” የዊዝጎ ላዉጠነዉዝ ሰቪዝጎ ጥውሽተነውድ ሚሪጝኩⶔ።

‎‎ ማኒ ፋክቸሪንግዝ፣ ቱሪዝምዝ፣ አይሲቲዝ፣ ኻትመዝመ ገጠርዙ አርሽነይ፣ አግልግለይዝ እኒዝጘም ኒግርንዙ ዚርፈኒዝ ዜገንዙ ቸልትዝመ አርየዙ በንትድ ሲሪየ ጻቨው ሰቪዙ አገነ ፋጥርሽኩ።

‎‎ሰቪዙ አገነ ፋጥርሸቊ ዜገን ማኽሊስ ንቕጸቊድ ውሸቭል ጛይ ተረቲዝም አይነተዝም ብላ ክልሊዝ ዜገንዙ ሰቭዙ አገነድ አውግረውዝ ሊጊሰናንስ ትኩርትዝ ሰራሸው አቐጘ ችጝነው ሚዝረድ ሚሪሰኩ።

‎‎ውሸቭሊዙ ሰቭዙ አገነ ኢትዮጵየዝ ነን ጽበው ኮሪዝ እቀጘዝ ቃውሰ ይውሽተው ኻለይዝመ ሰራሸቊ ውሸቭልድም ላውጥሸነዊል ችጝሽጘኩ ይና እጝቅም ጽይነው ሰቪዝ ፈኑ አናንስ አትርን ሰራሽን ላውጥሽነ ይናጙ ይነ ጽፈሽድ ኻትኑን ዲግ አጥን!

አመልማል ተድላ

የካቲት 30/2018

- Advertisement -spot_img
- Advertisement -spot_img

Latest article

AMECO Himitgna