እስካዊ ክብሩ ዎሰን ዌና አትሌት

ታደለ አጋጄ

ለንደንዳ ካስጙኽ ማራቶኑ ልኺትጚዳ አባላምቲ ጊዝስ ማራቶንዳ ልኺትጙኽ አትሌት ዮሚፍ ከጀልቻ ልኺትጜ 2ሳታዴስ ኩክራ ቱጝስ ካሉኽ አባላምቲ ይቶፒያው አትሌት ያኻ:: ታሪክስ አባላምቲ ጊዝስ ማራቶኑ ልኺትጚዳ አሴቴፍጙኽ ዮሚፍ ከጀልቻ 2ንቴ አቾ እሜማ ልኺትጜ አሌድጝስ ቱኽ ሳትኪላ 1 ሳት 59 ደኪኪስታ 41 ሴኮንድስ እስካዌ ክብረ ዎሰኖ ሜዜጌብፃ::

ቢቢሲው ንባርታጊ ፌይኹ አሜቱ ለንደኑ ማራቶኑ ዊፃንቲ ሳባስቲዮን ሳዌ 1 ሳት 59 ደኪኪስታ 30 ሴኮንድስ እቺቶ አሌድጝስ ካፅኹ ሳት እሺኾ:: 30 አሜቲ አትሌት ሳባስቲያን ሹኻ አሜታዴስ ፍና ጛው አጌሩ አትሌትስ ኬልቪን ኪፕቱምስ እምስታሺኹሳ 2 ሳት 00 ደኪኪ 35 ሴኮንዱሳ ክብረ ዎሴኖ ኬሽጝፅጝስ ታሪኮ እንፃኽስታ::

አትሌት ዮሚፍ ከጀልቻ 3000 ሜትሩ ሜሴናክሉ ልኺትጚዳ አቕስታው ያኹስ ኦሎምፒኩ ልኺትጚዳ ዴሜካ 10 ስታ 5 ሻይ ሜትሩ ልኺትጚዳ አሴቴፍጝጝስ ልኺትጛው አትሌትያኽ:: እሊት ይቶፒያት አትሌታ ትግስት አሰፋ ለንደኑ ማራቶንዳ ኔጌስቱት አትሌታ ታኻ:: አትሌት ትግስት አሰፋ ክብረ ዎስኖ ኬሽጝፅጝስ ሲፍጝጚስ ላጛንቲ ጊዝስ ለንደኑሳ ማራቶኖ ዊፃንታ ታኹት አትሌታኽ:: አትሌታ ልኺትጜ አሌድጝስ 2 ሳታ 15 ደኪኪስታ 41 ሴኮንድስ ቱጝስ ካሌ:: ንባርኪ ኢቢሲ ስፖርትዴስ አግፅንኹያ

አብን

AMECO Cherbewa