አምባ ላይ የነገሠው የታሪክ መዘክር፤ የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግሥት !

0
30

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በተወዳጇ የደሴ ከተማ ጀሚ ተብሎ በሚጠራ ኮረብታ አናት ላይ የሚገኘው የንጉሥ ሚካኤል ቤተ መንግሥት ግዙፉን የአይጠየፍ አዳራሽ፤ የልጅ ኢያሱ እልፍኝ፤ የራስ እምሩ ችሎት ቤት እና የንጉሥ ሚካኤል የጸሎት ቤትን አካቶ የያዘ ታሪካዊ ቦታ ነው፡፡

ከእነዚህ ቅርሶች መካከል በ1907 ዓ.ም በመገንባት የደሴ ከተማን ዘመናዊ ታሪክ የሚጋራው የአይጠየፍ አዳራሽ ዝነኛው ቦታ ነው፡፡ አይጠየፍ ከረጅም ጊዜ ዕደሜ ቆይታው ባሻገር የሀገራችንን የሥነ-ሕንጻ ሥራ እና የጥበብ እድገት ጠቋሚም ነው።

ቀደም ባለው ዘመን የነበረውን የግብር ሥርዓት እና አንድነት የሚዘክር በመኾኑ ታሪካዊ ፋይዳው ጉልህ መኾኑን ከቪሲት አማራ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#አሚኮ #ቱሪዝም #ንጉሥ-ሚካኤል-ቤተመንግሥት#አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here