የአገው ፈረሰኞች በዓል አከባበር የማለዳ ድባብ

    0
    29

    ባሕር ዳር: ጥር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአገው ሕዝብ ዘንድ ፈረስ የማንነት መገለጫ፣ የጀግንነት አርማ እና የታሪክ ምሰሶ ተደርጎ ይወሰዳል። ፈረስ እና ፈረሰኛነት ከአገው ሕዝብ የአኗኗር ዘይቤ፣ ከማኅበራዊ መስተጋብር እንዲሁም ለሀገር ከተከፈለ አኩሪ የጀግንነት ታሪክ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው።

    የአገው ሕዝብ ለፈረስ ያለው ክብር የሚመነጨው በጦርነት ጊዜ ታማኝ ጓደኛ፣ በሰላም ጊዜ ደግሞ የክብር፣ የጌጥ እና የዝና መገለጫ በመኾኑ ነው። በየዓመቱ የሚከበረው የፈረሰኞች ባሕል ይህንን ጥልቅ ትስስር በግልጽ የሚያሳይ ነው።

    በተለይም ጠላት ሀገራችንን ለመውረር ጦር ባዘመተበት ወቅት ጀግኖች አርበኞች በፈረሶቻቸው ታግዘው የጣላትን ቅስም ሰብረውበታል። በጦርነቱ የአገው ጀግኖችን እና የፈረሰኞቻቸውን ተጋድሎ ለመዘከር እንደተመሰረተ የሚነገርለት የአገው ፈረሰኞች በዓል 86ኛ ዓመቱን በዛሬው ዕለት ያከብራል።

    ክብረ በዓላቸውን የሚያደምቁት ፈረሰኞችም በጠዋቱ በእንጅባራ ጎዳናዎች እየተዘዋወሩ ትርኢታቸውን እያሳዩ ወደ ሜዳ በመውረድ ላይ ናቸው።

    የባሕል አምባሳደር የኾኑት የባሕል ቡድኖች እና የእንጅባራ እና አካባቢው ወጣቶች በባሕል አልባሳት አሸብርቀው በዓሉን በጠዋቱ አድምቀውታል።

    ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

    የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
    👇👇👇
    https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

    ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

    LEAVE A REPLY

    Please enter your comment!
    Please enter your name here