ድንቅ የተፈጥሮ ምድር እና ሀብት የኢላላ ጥብቅ ደን 🌿🌳

0
25

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ)
​በአማራ ክልል ከሚገኙ ጥብቅ ደኖች መካከል ተጠቃሽ የኾነው የኢላላ ደን፣ የተፈጥሮን እውነተኛ ውበት የታደለ እምቅ ሀብት ነው።

​📍 መገኛ ቦታው፦
ጥብቅ ደኑ በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በጓንጓ ወረዳ ይገኛል። የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ተወካይ ኅላፊ ወለሊ ጌቴ ደኑ ከቻግኒ ከተማ አሥተዳደር 17 ኪሎ ሜትር፣ ከእንጅባራ ከተማ ደግሞ 74 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

🌳🌲ኢላላ ጥብቅ ደን፦

✍️ 10 ሄክታር መሬት ይሸፍናል።

✍️ሁሌም ለዕይታ የሚስብ፣ የለመለመ እና አረንጓዴ የኾነ አስደናቂ ምድር ነው።

✍️ጥቅጥቅ ያሉ ረጃጅም ሀገር በቀል የተፈጥሮ ዛፎችን የያዘ ሲኾን እንደ ሰሳ፣ ግራር እና ሌሎችም ይገኙበታል።

📌🐒 የዱር እንስሳት መጠለያ ኾኖ እያገለገለም ይገኛል።

በውስጡም፦ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ጉሬዛ፣ ድኩላ እና ሌሎች የዱር እንስሳት ይኖሩበታል።

📌🦜 የተለያየ ዝርያ ያላቸው ውብ የአዕዋፍ ዝርያዎች መገኛም ነው።

📌🌍 ደኑ የአካባቢውን የሥነ-ምኅዳር ሚዛን በመጠበቅ ረገድ ሚናው የላቀ ነው።

​ቦታው ድንቅ የተፈጥሮ ምድር እና ሀብት መኾኑን የገለጹት አቶ ወለሊ፤ የአካባቢው ማኅበረሰብ ደኑን “የራሴ የግል ሀብት ነው” በሚል ስሜት ያለማንም ተፅዕኖ በባለቤትነት እየጠበቀው እና እየተንከባከበው እንደሚገኝ ያስረዳሉ።

የደኑ መኖር የአካባቢው የአየር ፀባይ ለሕዝቡ ምቹ እንዲኾን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህንን የተፈጥሮ ፀጋ ይበልጥ በመጠበቅ፣ አካባቢውን ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

#አሚኮ_ዜና #ቱሪዝም_አማራ_ክልል #አዊ #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here