የጣና ሐይቅ ውበቶቹ! “ፔሊካኖች”

0
69

 

​ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ ጣና ሐይቅ ሰማያዊ ድባብ ያለ እነሱ ሙሉ አይኾንም።

ፔሊካኖች ያንን ግርማ ሞገስ የተላበሰ እና በበረዶ የተለወሰ የሚመስል ነጭ አካላቸውን እና እንደ ንጋት ፀሐይ ፈካ ያለ ቢጫ ምንቃራቸውን ይዘው በውኃው ላይ ሲንሳፈፉ ጣና ሐይቅ በውበት ላይ ውበት ይደርባል።

ሰፊ ክንፎቻቸውን ዘርግተው በጣና ሰማይ ላይ ሲቀዝፉ የተፈጥሮ ምስጢር በጣና ላይ ይገለጻል።

​ውበታቸው ብቻ ሳይኾን ለጣና ያላቸው ታማኝነትም ልዩ ነው። ሁልጊዜም በዚያው ባልተለወጠ ታማኝነት እና ፍቅር ይኖራሉ።

ከሐይቁ ዓሣ አጥማጆች ጋር ያላቸው ጥምረት፤ እርስ በርስ በቡድን የሚኖራቸው መስተጋብር እና ስምምነት የሰላም እና የጽናት ተምሳሌት ያደርጋቸዋል።

​በሰመሃል ፍስሐ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here