አስደናቂው የተፈጥሮ ፍል ውኃ – አዋይቱ

0
32

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከአዲስ አበባ 26ዐ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ሰንበቴ ከተማ ምሥራቅ አቅጣጫ አራት ኪሎ ሜትር ጉዞ በኋላ የሚገኝ ድንቅ የተፈጥሮ መስህብ ነው፡፡

አዋይቱ የተፈጥሮ ፍል ውኃ በስፋት መታወቅ የጀመረው በ1953 ዓ.ም እንደኾነ ይነገርለታል፡፡ አዋይቱ ፍል ውኃ በአጣዬ ናዛሮና ሰንበቴ ቀቢ ወንዞች መገናኛ ውስጠኛው ማዕዘን ላይ በአራት ኮረብታዎች ተከቦ ይገኛል፡፡

አለታማ ከኾነው መሬት ውስጥ የሚወጣው እንፋሎት ከነጐድጓዳማ ድምፁ ጋር ተዳምሮ ለአካባቢው ልዩ ውበትን አጐናፅፎታል፡፡ በፍል ውኃው ዙሪያ ደጋጋ፣ ኮሎ፣ አያበር እና አጐብዲ የተባሉ አራት ኮረብታዎች ይገኛሉ።
የፍል ውኃው መገኛ ቦታ ከሩቅ ሲመለከቱት ዙሪያው በአረንጓዴ እፅዋት የተሸፈነ እና የተነደፈ ጥጥ መስሎ ነው የሚታየው፡፡

የተፈጥሮ ፍል ውኃው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ያለው ከ1ዐ እስከ 15 ደቂቃ ባለው የጊዜ ርዝማኔ ሥጋ፣ በቆሎ እና እንቁላል የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን ያበስላል፡፡ ከፍል ውኃው ውስጥ እየተንተከተከ የሚወጣው ጭስ ሰዎች የደከመ ሰውነታቸውን ለማፍታታት፣ ውበታቸውን ለመጠበቅ እና ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ እንደሚጠቀሙበት ይነገራል።

ፍል ውኃውን የጤና ጠቀሜታ ለማጥናት ወደ ቦታው የሚሄዱ በርካታ ባለሙያዎችን ጨምሮ ባለፋት ዓመታት የሀገር ውስጥ ጐብኝዎች ተመልክተውታል፡፡ መረጃው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here