የባሕል እና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ውድድር በደሴ ከተማ ተጀመረ።

0
59
ደሴ: ታኅሣሥ 22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ባሕላችን ለሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት 17ኛው የደቡብ ወሎ ዞን ባሕል እና ኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ውድድር በደሴ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ፌስቲቫሉ ከታኅሣሥ 22 እስከ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በደሴ ከተማ ወሎ ባሕል አምባ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከናወናል።
በመርሐ ግብሩ ባሕላዊ ውዝዋዜዎች፣ ቲያትሮች፣ የዕደ ጥበብ እና ቁሳዊ ውጤቶች ኤግዚቪሽን እንዲሁም ሌሎች ኪነ ጥበባዊ ትርኢቶች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
ከዞኑ 20 ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ቱባ ባሕል እና ታሪካቸውን ያቀርባሉ ተብሎም ይታሰባል።
ዘጋቢ:- መስዑድ ጀማል
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here