አሚኮ የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።

0
48
ጎንደር: ጥር 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ ለጎንደር እና ለአካባቢው ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ያስችል ዘንድ አሚኮ ጎንደር ስቱዲዮን ወደ አገልግሎት ማስገባቱ ይታወሳል። አሚኮ በአካባቢው ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ ነው።
የሰሜን ጎንደር ዞን ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ አስራት ክብረት አሚኮ የጎንደር ስቱዲዮን መክፈቱ ለጎንደር እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ቀልጣፋ እና ተደረሽ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል ብለዋል።
ስቱዲዮው አገልግሎት መስጠት በጀመረበት ጀምሮ ዘገባዎች ወቅታዊነታቸውን ጠብቀው ሲስተናገዱ መቆየታቸውንም ተናግረዋል።
አሚኮ ተቀዛቅዞ የነበረውን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት እና በዞኑ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማስተዋወቅ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል።
ሰሜን ጎንደር ዞን የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ መገኛ በመኾኑ የፓርኩን መስህብ በማስተዋወቅ እና የጥበቃ ሥራውን ማጠናከር በሚያስችሉ ተግባራት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ሲሠራ መቆየቱንም አብራርተዋል።
የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተዎካይ ላቀው መልካሙ አሚኮ የፓርኩን መስህብ ከማስተዋወቅ ባለፈ በዘላቂነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ ጉዳዮችን በማስገንዘብ በኩል ወቅታዊ እና ተደራሽ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል። ላበረከተው አስተዋጽኦም ምሥጋና አቅርበዋል።
አሚኮ ተደራሽነቱን ለማሻሻል ቅርንጫፎቹን በማስፋት እና የዞን ሪፖርተሮችን በመመደብ ለቱሪዝም ዘርፉ መነቃቃት እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በቀጣይም የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here