ኑ ጥምቀትን በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እናክብር።

0
58
ባሕር ዳር: ጥር 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቱሪዝም ሚኒስቴር በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት መልዕክት ኑ ጥምቀትን በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ እናክብር ብሏል።
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናት ብቻ እንደቀሩት ገልጿል።
በየአድባራቱ የሚሰማው የመንፈሳዊ ዝግጅት ድምፅ፣ እንደ አዲስ በኮሪደር ልማቱ የደመቁ የሀገራችን መንገዶች እና እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች የምትገኘው ኢትዮጵያ ለየት ያለ ድባብ ውስጥ ትገኛለች ነው ያለው።
ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ፤ በታሪካዊቷ ጎንደር፣ ባቱ፣ በላሊበላ፣ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ፣ አክሱም፣ ጋምቤላ እና በመላው ሀገሪቱ የሚታየው ይህ ድንቅ ትዕይንት ለዓይን ማራኪ፣ ለነፍስ ደግሞ ረፍት የሚሰጥ ነው ብሏል።
የካህናቱ በያሬዳዊ ዜማና በሽብሸባ፣ ምእመናኑ ደግሞ በባሕላዊ ውዝዋዜና በደስታ ታቦታቱን አጅበው ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚጓዙበት ቀን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
እርስዎስ ይህን መንፈሳዊ እና ባሕላዊ ትዕይንት የት ኾነው ለማክበር አቅደዋል? ኑ! ጥምቀትን በምድር ቀደምቷ ኢትዮጵያ እናክብር ብሏል በመልዕክቱ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here