የታሪክ ማህደሯ ከተማ ልጆች እንግዶቻቸውን ተቀብለው ለማቀማጠል ተዘጋጅተዋል።

0
14
ባሕር ዳር፡ ጥር 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በየዓመቱ ጥር 25 የሚከበረው የቅዱስ መርቆርሬዎስ በዓል የደብረታቦር ከተማ አንዱ የድምቀት ምንጭ ነው። የበዓሉ መዳረሻ እና ዋዜማ ቀደም ብሎ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
“ፈረስ በኢትዮጵያ፣ ደቡብ ጎንደር እና በደብረ ታቦር እና የቅዱስ መርቆርሬዎስ በዓል ከበዓልነት ባለፈ ለምጣኔ ሀብት ምንጭ” የሚል ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በዛሬት ዕለትም የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መልዕክት የከተማዋን የኢንዱስትሪው ዘርፍ የበኩር ጠንሳሽነት የሚያመላክት የጎዳና ላይ ትርዒት አካሂዷል።
በነገው ዕለት ደግሞ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀጥሉ ሲኾን ጥር 25 በመልኩ ልዩ የኾነው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል በአጅባር ሜዳ ይደምቃል። ፈረሶች እና ፈረሰኞቹም ለዐይን የሚያፈዙ ትዕይንቶችን ለማሳየት ዝግጁ ኾነዋል።
የታሪክ ማኅደሯ ከተማ ነዋሪዎች እንግዶቻቸውን ተቀብለው ለማቀማጠል ጓዳቸውን ሁሉ ሞልተው፣ ከተማቸውንም አስውበው እየተጠባበቁ ነው።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here