የጣና ሐይቅ ጌጦች

0
77
ባሕር ዳር: መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጣና ሐይቅ ገጽታ ላይ ልዩ ድምቀት የሚሰጡት እና ባለ ግዙፍ መንቁር የውኃ ላይ ወፎች የኾኑት ፔሊካኖች የሐይቁ ተፈጥሯዊ ውበት መገለጫዎች ናቸው።
እነዚህ ነጫጭ ወፎች በሐይቁ ዳርቻ ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ለጎብኝዎች ልዩ የዕይታ ሐሴትን እየፈጠሩ ይገኛሉ።
👉 የፔሊካኖች ተፈጥሯዊ ባህሪ
ፔሊካኖች ከረጢት በሚመስል ጉሮሯቸው እና በረጅም መንቁራቸው የሚታወቁ ሲኾን በውኃ ላይ የመጓዝ ብቻ ሳይኾን ጠንካራ ጠላቂ ዋናተኞችም እንደኾኑ እና የወፎች ሳይንስን (ሳይንስ ኦፍ በርድ) ይተነትናል።
እነዚህ ወፎች እስከ 25 ዓመታት የመኖር ዕድሜ አላቸው።
ዋነኛ ምግባቸው ዓሳ ሲኾን ሌሎች አነስተኛ የውኃ ውስጥ እንስሳትንም ይመገባሉ።
በሐይቁ ላይ ዓሳ ሲያድኑ እና ሰፋፊ እግሮቻቸውን ተጠቅመው ውኃው ላይ ሲንሸራሸሩ የሚያሳዩት ትዕይንት ለተመልካች ልዩ እርካታን ይሰጣል።
ፔሊካኖች ከተፈጥሯዊ ውበታቸው ባለፈ በቅዱሳት መጻሕፍት ዘንድ የፍጹም ደግነት እና የመሥዋዕትነት ምሳሌ ተደርገውም ይጠቀሳሉም።
በተለይም እናት ፔሊካኖች ለልጆቻቸው ያላቸው ርህራሄ የሚደነቅ ነው። ልጆቻቸውን ለመመገብ ጥረት አድርገው ምግብ ሲያጡ፣ ለልጆቻቸው ደኅንነት ሲሉ ራሳቸውን አሳልፈው እስከመስጠት መስዕዋትነት ይከፍላሉ። ይሄውም ራሳቸውን አድምተው ለልጆቻቸው ይመግባሉ።
ወደ ጣና ሐይቅ የሚዘልቁ ቱሪስቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በእነዚህ ነጫጭ ወፎች ትዕይንት ተፈጥሮን ለማድነቅ ዕድል ያገኛሉ። ፔሊካኖቹ ከሐይቁ ሥነ ምሕዳር ጋር ተስማምተው መኖራቸው የጣናን መስህብነት ይበልጥ አጉልቶታል።
በምስጋናው ብርሃኔ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here