አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ ልማት ፕሮጀክትን ይጎበኛሉ።

0
11

 

#ባሕር_ዳር ፡ ሰኔ 26/2018 የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ ልማት ፕሮጀክትን ይጎበኛሉ።

በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ የተመራ ቡድን ላሊበላ ከተማ የገባ ሲሆን፤ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች በቡድኑ ውስጥ ይገኙበታል።

ቡድኑ በላሊበላ ቆይታው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እና የተለያዩ ስፍራዎችን ከመጎብኘት ባለፈ፤ የላሊበላ ቅርሶች ዘላቂ የልማት ፕሮጀክት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ ይመለከታል።

የላሊበላ ቅርሶች ለዘላቂ ልማት ፕሮጀክት ለጎብኚዎች የሚሆን መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚያተኩር ሲሆን አስቸኳይ የቅርስ ጥገናን ያካትታል።

የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት በዓለማችን ከፍተኛ ተጓዦች ከተመረጡ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባሕል ተቋም (ዩኔስኮ) ምርጥ አምስት ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here