የሰሜን ጎንደሯ ፈርጥ ደባርቅ ከተማ!

0
15
ደባርቅ ከተማ የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን ለመመልከት የሚመጡ ጎብኝዎች ማረፊያ ናት።
ከተማዋ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በደጃች አምሳለ ዘሴ እንደተመሠረተች የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ።
ከተማዋ ከስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በቅርበት እና ከአስደናቂው የሊማሊሞ መንገድ አናት ላይ ትገኛለች።
ከጎንደር ወደ ሽሬ፤ ከሽሬ ወደ ጎንደር ጉዟቸውን የሚያደርጉ መንገደኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለመጎንጨት ማረፊያቸውን ደባርቅ ከተማ ላይ ማድረጋቸው የተለመደ ነው።
ከተማዋ ለጎብኝዎች ምቹ ማረፊያ እንዲትኾን፤ ገጽታዋ እንዲገነባ እና ውበቷ እንዲጎላ የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የኮሪደር ልማትን አስጀምሮ እየሠራ ይገኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here