ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ኅዳር ያሉት ወራት የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ መልኮች የበለጠ ተገልጠው ውብ የሚኾኑበት ነው። በመኾኑም ወቅቱ አካባቢውን ለመጎብኘት ከሚመጡት ምርጥ ጊዜያት አንዱ ነው።
መልክዓ ምድሩ አረንጓዴና እጅግ ማራኪ ነው፣ ፏፏቴዎቹ ንጹህ እና ነጭ ኾነው ቁልቁል ሲወረወሩ መንፈስን ይገዛሉ። በቀለማት ያሸበረቁ የደጋ አበቦች ለተራራዎች የበለጠ ውበት ያስተጋባሉ።
በዚህ ወቅት በርካታ ቱሪሰቶች በግል እና በቡድን እየኾኑ ወደቦታው እንደሚያቀኑ የፓርኩ ጽሕፈት ቤት መረጃ ይጠቁማል። በተለይም በመስከረም በስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ መገኘት በእነዚህ አስደናቂ መልክዓ ምድሮች ውስጥ ተፈጥሮን ለማድነቅ፣ ብርቅየ የዱር እንስሳትን በየአይነቱ ለማየት፣ የነፋሻውን ተራራ ንጹህ አየር ለመተንፈስ ያስችላል።
#አሚኮ #Tourism #Ethiopia
ባሕርዳር #መስከረም06/2018 ዓ.ም









