የፋሲለደስ ግንብ አምሳያው የወልቃይቱ አያና ዕዝጊ ቤተ መንግሥት።

0
54
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር አብያተ መንግሥታት አምሳል ተገንብቷል።
ለበርካታ ዓመታት ትኩረት ባይሰጠውም ዛሬም ድረስ የኪነ ሕንጻው ቅሪተ አካል በቤት ሞሎ ከተማ አሥተዳደር ከፍታ ላይ በግርማ ተኮፍሶ ይታያል።
ይህ የታሪክ አምባ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ በካፋ ዘመነ መንግሥት እንደተገነባ ይነገርለታል።
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በቤት ሞሎ ከተማ አሥተዳደር የሚገኘው የአያና ዕዝጊ ቤተ መንግሥት።
በወቅቱ የነበሩት ደጅ አዝማች አያና ዕዝጊ የዱር እንስሳት አዳኝ እና ቀስተኛ ስለ ነበሩ ከአጼ በካፋ ጋር በወልቃይት አካባቢ አደን በጋራ ያድኑ እንደነበር ታሪክ ያነሳል።
ደጅ አዝማች አያና ዕዝጊ ከተከዜ እስከ ሱዳን ያለውን መሬት ያሥተዳድሩ እንደነበርም ሰነዶች ምስክር ናቸው።
አጼ በካፋ ለደጅ አዝማች አያና ዕዝጊ ከሱዳን አዋሳኝ ያለውን ድንበር ይጠብቅ ዘንድ በእርስት እንደሰጡት የወልቃይት ጠገዴ ታሪክ አዋቂው አለቃ ወረደ ኃይሌ በአንድ ወቅት ከአሚኮ ጋር ባደረጉት ቆይታ አንስተዋል።
ኪነ ሕንጻው በወቅቱ በእንቁላል እና ወተት እንደተገነባ ይነገራል ሲሉም ተደምጠዋል። የአያና ዕዝጊ ቤተ መንግሥት ሞሎ በሚባል ባለሙያ በመገንባቱ ከተማዋ ቤት ሞሎ ተብላ እንደተሰየመችም አንስተዋል።
ኪነ ሕንጻው ከጎንደር አብያተ መንግሥታት ጋር እንደሚመሳሰል ያነሱት አለቃ ወረደ ኃይሌ በወቅቱ ከጎንደር ሕዝብ ጋር ጠንካራ የሕዝብ ግንኙነት እንደነበር በአጽንኦት አንስተዋል።
ታሪክ የትናንት መነሻ ናቸውና ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል። የትናንት ማንነት ማሳያዎች ከነ ታሪካቸው እና ከነ እሴታቸው ለትውልድ ይተላለፉ ዘንድም ሁሉም ይመለከተዋል። ሰላም!
በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here