ባሕል እና ታሪክ ለዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት! 🇪🇹

0
43

‎
በአማራ ክልል የሚገኙ የባሕል፣ የታሪክ እና የቱሪዝም ሃብቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ሥራዎች በውጤታማነት እየተከናወኑ ነው። የአማራ ክልል ባሕል ኪነ-ጥበብ እና ዝክረ ታሪ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ገብረማርያም ይርጋ እ.ኤ.አ ከ2023 እስከ 2026 በተካሄዱ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫሎች የክልሉን ባሕል እና ታሪክ በማስተዋወቅ ረገድ ብዙ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። ባሕል እና ታሪክን ከማስተዋወቅ ባለፈ የሕዝብ ለሕዝብ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በማጠናከር ረግድ ትልቅ ሚና እንዳለውም ነው የተናገሩት። እነዚህ የባሕል እና የታሪክ መድረኮች አርቲስቶች ችሎታቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ሙያዊ ብቃታቸውን እና የፈጠራ ክህሎታቸውን በትልቅ መድረክ ላይ በማሳየት ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።​ ከሌሎች ሀገራት ባሕሎች ከተውጣጡ አርቲስቶች ጋር የመገናኘት፣ የመማማር እና የልምድ ልውውጥ የማድረግ ዕድል ይፈጥርላቸዋል።በማዕከሉ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ የክልሉን ታሪካዊ ቅርሶች፣ ባሕላዊ አልባሳት፣ ኪነ-ጥበብ እና ትውፊቶችን ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የማስተዋወቅ ሥራ ተከናውኗል ብለዋል። በሀገር ውስጥ በሚካሄዱ ዝግጅቶች የክልሉን ባሕል ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር የማስተዋወቅ እና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅም የውጭ ጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሠራ እንደኾነ ገልጸዋል። ‎​ባሕል እና ታሪክን ማስተዋወቅ የሀገርን መልካም ገጽታ ከመገንባት ባለፈ የዲፕሎማሲ ግንኙነትን የሚያጠናክር እና ቱሪዝምን የሚያስፋፋ ውጤታማ መንገድ ነው።

#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

✍️ በጌጤ ደፋሩ (ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአሚኮ የተግባር ተማሪ)

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here