በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የምትገኝ የገጠር መንደር ናት
የምታከብረው የጥምቀት በዓል ግን ከበርካታ ታላላቅ ከተሞች የሚገዝፍ ነው
በዓሉ መከበር የጀመረው ከ600 ዓመታት በፊት በ14ኛው ክፍለ ዘመን ነው
በሸንኮራ ወንዝ ላይ የሚከበረው የኢራንቡቲ ጥምቀት በአጼ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ደማቅ የጥምቀት በዓላት አንዱ እንደነበር ይነገራል
👉 44 ታቦታት ወደ ባሕረ ጥምቀት ይወርዳሉ
👉 በምዕመናን ታጅበው በተለያዩ አቅጣጫ ረጅም ርቀትን አቆራርጠው ታቦታቱ የኢራንቡቲ ባሕረ ጥምቀት ሲደርሱ ትንሿ የገጠር መንደር ትደምቃለች
ምንጭ፡- አማራ ድንቅ ምድር መጽሐፍ