ባሕር ዳር፡ የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አንጎለላ ሰሚነሽ ጽርሐ-አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ኪዳነ-ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ከተለያየ የሀገራችን አካባቢዎች የተሰባሰቡ በርካታ የሃይማኖት ተጓዦች በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።
አንጎለላ ከደብረ ብርሃን ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክ እና የጦር አበጋዙ ፊታውራሪ ገበየሁ የተወለዱባት ታሪካዊ ቦታ ናት። መረጃው የቪዚት አማራ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!